Tuesday, August 16, 2016

በቤተ እስራኤላውያን ስም የሚነግደውን የወያኔ ሚዲያ ቤተ እስራኤላውያን እያጭበረበረ ስለሚገኝ ልናስቆመው ይገባል


ብዙሃኑ ቤተ እስራኤላዊ የጎንደር ህዝብ ነው ባልሳሳት 95 ፐርሰንቱ በ እስራኤል የሚገኘው ያማለት ከ 147 ሺህ ቤተ እስራኤላዊ እስራኤል ከሚገኙት 140 ሺውን ያህል ይይዛል.. 9 ሺህ ያህል ቤተ እስራኤላውያኖች አሁንም በጎንደርና በአዲስ አበባ ይገኛሉ ሆኖም ግን አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው የአንድ አናሳ ብሄር የበላይነትና የማናለኝበት አሸባሪያዊ ስርዓት ብዙ የአማራና የ ኦሮሞ ልጆች በግፍ ሲገደሉ የአለም ታላላቅ ሚዲያዎች ዘግበውታል ።
እስራኤል የሚገኘው ቤተ እስራኤላዊ በግፍ ስለሚገደሉት ወንድሞቹና እህቶቹ በተለይ የቋንቋ ችግር ያለባቸው ወላጆች I ETV ን እንደ መረጃ ምንጭ በመጠቀም ብዙ ወላጆችትክክለኛ መረጃ ለመስማት ፈልገው ነበር ነገር ግን ይሄው ብጥብጡ ከተቀሰቀሰ ጀምሮ በአቶ ፋሲል ለገሰ የሚመራውና እንዲያውም ከ እስራኤል መንግስት ለቤተ እስራኤሎች ተብሎ ድጎማ የሚደረግለት ይሄው ቻናል ይባስ ብሎ ሌላ ሁለተኛ ኢዮጵያ የምትባል አገር እንዳለች ሁሉ ስለ “እድገት” ይዘግባል ምንም አይነት መረጃ ሳይሰጥ እንዲያውም የኢትዮጵያውን አምባሳደር በ እስራኤል “ክቡር አቶ ህላዊ ዮሴፍ ” እያለ ሰኞና ማክሰኞ ህዝብን ባሰለቸመልኩ እያቀረበ ያናዛቸዋል .አቶ ህላዊ ዮሴፍም መድረኳን ተጠቅመው ስለ ወያኔ “ብልጽግና ዲሞክራሲያዊ” ወ.ዘ.ተ ተናግረውባት ይሄዳሉ እሳቸው ምን አጠፉ የቤተ እስራኤሉን የ አየር ስዓት ለፖለቲካዊ ፍጆታ ይጠቀሙበታል ።
.. አሁንም ቢሆን ሁሉም ቤተ እስራኤላዊ በመካከለኛው ምስራቅ ብቸኛዋ ነፃነት ከሰፈነባት ዲሞክራሲያዊቷ እስራኤል ቁጭ ብሎ ይህን ያህል ህብረተሰቡን በናቀ መልኩ ስለኢትዮጵያ “እድገትና በአለም በኢኮኖሜ የበለፀገች “አገር እያለ ይዘግባል ። ነገሩ እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው ” ያም ሆነ ይሄ” ትላለች አንዲት ወዳጄ… መፍትሄው ትኩሱን የወጣት ሃይል አደራጅቶ ከተቋማት ላይ ተቋማት በመገንባት መላው ቤተ እስራኤላዊ በአንድነት ለነፃ ሚዲያ እንዲነሳና ይህን የወያኔ ፕሮፖጋንዳ ነዢ ቻናል አዘግቶ .. ከሁሉም የነጻ ..ነፃ ሚዲያ መክፈት ነው ….ሌላው እንደመፍትሄ መወሰድ ያለበት እርምጃ ሁሉም ቤተ እስራኤላዊ ከቤቱ ይህን ዘረኛ ቻናል ማስወገድ ይኖርበታል ያኔ ከሳተላይት የ ሆት ካምፓኒም ሆነ የ የስ ካምፓኒ ያባሩታል። ድል ነፃ መረጃ ለተከለከለው ቤተ እስራኤል … (አገር ሰላም)
በቤተ እስራኤላዊ ስም የሚነግደው አሳማ ይሄ ነው
በቤተ እስራኤላዊ ስም የሚነግደው አሳማ ይሄ ነው

No comments:

Post a Comment