አትላንቲክ ካውንስል ለአፍሪካ Atlantic Council for Africa የተሰኘው የአሜሪካ የመንግስታትና የአለም አቀፍ ተቋማት ምክር ቤት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበርና የመድረክ ም/ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲናን እና የሰማያዊ ፓርቲን ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነትን በማነጋገር ላይ ናቸው። ለስብሰባ የተጠሩት በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው አሳሳቢ የፖለቲካ ቀውስና ሀገሪቷን ያለምንም አማራጭ የፖለቲካ አመለካከት በወታደር ሀይል በመቆጣጠር በውጥረት ላይ ስለሚገኘው የኢህአዴግ ስርዓት ማብራሪያ ሰጥተዋል። የዩናትድ ስቴትስ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ችግር እና በተለይ በነፃ ሚዲያውና ተቃዋሚዎች ላይ ሰለሚደርሰው ወከባ ሙሉ ግንዛቤ እንዳለው አሳውቀዋል።
በስብሰባው ለይ ከተገኙትና ስማቸው በተቋሙ ይፋ ከሚደረጉት መካከል በዩናይትድ ስቴትስ የወጪ ጉዳይ አማካሪዎች፣ የፔንታጎን መካላከያ አማካሪዎች፣ የፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የጸጥታ ዋና አማካሪ በቦታው የተገኙ ሲሆን በቦታውም ሌሎች የአሜሪካን ምሁራን ተገኝተዋል። ከዚህ በፊት ስማቸው የሚታወቁት አምባሳደር ዴቪድ ሺን፣ ሃርማን ኮኸን እና የግጭትና ስትራቴጂ ምሁር Terrence Lyons (Conflict Analysis and Resolution expert) እና ሌሎች ስማቸው እንዳይጠቀስ የሚፈልጉ ዲፕሎማቶች በቦታው ተገኝተዋል። የውይይቱ ርዕስ ያተኮረው ዩናይትድ ሰቴትስ ከኢትዮጵያ የሚታገኘው ስትራቴጂክና ወታደራዊ ጥቅሞች ሳይነኩ እንዴት አዲስ የአደራ መንግስት (Caretaker Government) ለማቋቋም እንደታሰበና በሂደት በምን አይነት ሁኔታ ሰላማዊ የስልጣን ክፍፍልና ሽግግር ማድረግ እንደሚቻል ለመምከር መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል። መረጃውን ምክር ቤቱ በከፊል ይፋ እንደሚያደርገው ተነግሯል።
No comments:
Post a Comment