በባህር ዳር የቤት ውስጥ የመቀመጥ ኣድማ ወደ ተቃውሞ ሰልፍ ተለውጦ ሕዝቡ አደባባይ ወጥቷል።ባለስልጣናት ተደብቀዋል።
በዳንግላ ከተማ የወረዳው አስተዳዳሪ ቤት ተቃጥሎአል። አንድ ዋና ሳጅን አየነው የሚባል በህዝብ ላይ በመተኮሱ የእሱም ቤቱ ተቃጥሎአል ። በአዴት ከተማ ፖሊሶች ከህዝብ ጋር በማበር እየተቃወሙ ሲሆን፣ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ተባብረው ከተማዋን በማስተዳደር ላይ ናቸው። በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ አርብ ገበያ አድማው ለሁለተኛ ቀን እየተደረገ ሲሆን፣ መንገዶች በመሉ በድንጋይና በግንድ ተዘግቷል። ህዝቡ የጎበዝ አለቃውን ነገ ተሰብስቦ ይመርጣል። በቋሪት አራት የጎበዝ አለቆች ከተማዋን እንዲያስተዳድሩ ተመርጠዋል። …ይልማና ዴንሳ(አዴት) ከተማ ሙሉ በሙሉ ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ህዝቡ ስልጣን ተቆጣጥሯል። ባሁኑ ሰአት ከተማዋ በጎበዝ አለቃ እየተመራች ነው። ቄሶችና ባለሃብቶች ከተማዋን ተረክበዋል።
No comments:
Post a Comment