Saturday, August 20, 2016

በመጪው አመት 2009 የተማሪዎች ንቅናቄ ይነሳል የሚል ስጋት ሕወሓት አድሮበታል::የተለመደው ስልጠና በ2009 መስከረም ይጀምራል::(ምንሊክ ሳልሳዊ)


በመጪው አመት 2009 የተማሪዎች ንቅናቄ ይነሳል የሚል ስጋት ሕወሓት አድሮበታል::የተለመደው ስልጠና በ2009 መስከረም ይጀምራል::(ምንሊክ ሳልሳዊ)
ከደህንነትና ስለላ ቢሮ የተገኙ መረጃዎች እንደሚተቁሙት በኢትዮጵያ የተነሳውና ከዳር እስከዳር የተቀጣጠለው የለውጥ ጥያቄ ሕዝባዊ የአብዮት ማእበል የመስከረም ወር የትምህርት ቤቶች መከፈትን ተከትሎ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ንቅናቄ ይነሳል በሚል ስጋት ለአስተማሪዎች ለወላጆችና ለተማሪዎችና ለትምህርት ባለሙያዎች ስልጠና ተዘጋጅቶ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል እንደሚሰጥ ታውቋል::ይህንን ስልጠና ለመተግበር ይረዳ ዘንድ ከደህንነት ቢሮ ለሽፈራው ሽጉጤ የተላለፈው መመሪያ መሰረት ያደረገ ስብሰባ በአዳማ ከተማ የጠቅላላ ትምህርት ዘርፍ ሀገራዊ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ በሚል እየተደረገ እንደሆነ ተጠቁሟል::ለዚህ ስልጠና የሚውል የአስራእምስት ቀን ከፍተኛ የአበልና የትራንስፖርት በጀት ከምግብ ጋር መመደቡ ተሰምቷል::
የደህንነት ቢሮ ለሽፈራው ሽጉጤ በላከው ትእዛዝ መሰረት መስከረም 3 2009 ጀምሮ ለ15 ቀናት አስተማሪዎች፣ ተማሪዎች፣ ወላጆችና የትምህርት ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ስልጠና በመላው አገሪቱ ሊሰጥ የታቀደ ሲሆን ሕወሓት በዚህ ስልጠና ተማሪዎችን እና ወላጆችን የማስፈራራት በመምህራን እና የትምህርት ባለሙያዎች ላይ ደሞ ተጽእኖ የሚፈጥር ሰነድ ያዘጋጀ ሲሆን በዚህ የስልጠና ሰነድ ላይ እንደከዚህ ቀደሙ ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተዘጋጀው ሰነድ በማሻሻል ተመሳሳይ የሆነ የፖለቲካ ስልጣን ማስረዘሚያ ቃላቶች የታጨቁበት መሆኑ ታውቋል::በመላው ኢትዮጵያ ያሉ አስተማሪዎች፣ ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች፣ ሁሉም የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ የትምህርት ባለሙያዎች እንዲሁም ወላጆች የሚሳተፉበት እንደከዚህ ቀደሙ በተለመደው መልኩ አፋቸውን ሊያሲዝልኝ ይችላል የሚል ስልጠና በሕወሓት ካድሬዎች ይሰጣቸዋል፡፡ ይህ ስልጣና ካልተጠናቀቀ ትምህርት እንዳይጀመር የደህንነት ቢሮ አዟል:: #ምንሊክሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment