Friday, August 26, 2016

ሕገመንግስቱ – ዛሬ ምን ተገኘ ? የኦሮሞን ሕዝብ ተቃውሞ ሕገወጥ ነው ብለው እየገደሉና እያሰሩ ያሉት ሕወሓቶች ናቸው።


ዛሬ ምን ተገኘ ? የኦሮሞን ሕዝብ ተቃውሞ ሕገወጥ ነው ብለው እየገደሉና እያሰሩ ያሉት ሕወሓቶች ናቸው።
ሃያ አምስት አመት የተለፋበት የጎሳ ፖለቲካ መክሸፉ የሕዝብ ኣንድነት ያስደነገጣቸው የሕወሓት ካድሬዎች የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ሕገወጥ ነው ያለ ኣካል ያለ ይመሰል ራሳቸው ሕገወጥ ነው እያሉ(የኦሮሞን ሕዝብ ትግል ህገ መንግሥታዊ ነው፣ሁላችንም ልንደግፈው ይገባል)እያሉ በማላዘን ላይ ናቸው በመጀመሪያ ደረጃ የኦሮሞ ሕዝብ ለተቃውሞ ሲነሳ የጠባቦች ሴራ የጋኔኖች የኣጋንቶች ተግባር ኣሸባሪው ኦነግና ጸረ ሰላም ሃይሎች የሚመሩት ነው በማለት በሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ልጆች ሲገደሉ በኣስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወደ ማጎሪያ ካምፖች ሲጓዙ ይህ ግድያና እስር ኣሁንም ኣልተቋረጥም ይህ ሁሉ ግፍ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ሲፈጸም ኢትዮጵያውያን ከኣለም ኣጽናፍ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ኣለም ኣቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ሲጮኹ የሕወሓትና ኣጫፋሪዎቹ መልስ ግን የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ሕገመንግስቱን ያልተከተለ ሕገወጥ የጋኔኖች ስራ ነው በማለት ከባድ ግፍና ሰቆቃ ከዘር ማጥፋት የማይተናነስ ተግባር እየፈጸሙ ይገኛሉ።የኦሮሞ ሕዝብ መብት ሕገመንግስታዊ ከሆነ ባለፉት ኣመታት የኦሮሞን ሕዝብ ሕገወጥ ነው ብሎ መግደል ማሰር ለምን ኣስፈለገ ? ዛሬ ምን ተገኘ ?
የኦሮሞን ሕዝብ ተከትሎ በሰሜን ኢትዮጵያ ሕወሓትን በሱሪው ላይ እያሸናው ያለው የኣማራው ሕዝብ ሲነቃነቅ በደል በቃኝ ብሎ ኣደባባይ ሲወጣ የኦሮሞ ሕዝብ ደም የኔም ደም ነው ሲል በሕዝቦች መካከል ቁርሾና ጥላቻ ለመፍጠር ሃያ ኣምስት ኣመት የተለፋበት የጎሳ ፖለቲካ መክሸፉ ሕወሓትና ግብረኣበሮቿን ኣስደንግጧል።
ከአስር አመት በኋላ ትግራይን ገንጥሎ ቀሪውን የኢትዮጵያ ክፍል በማይበርድ የርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ከቶ በዘረፉት ገንዘብ ትግራይን ለማስተዳደር ያለሙት የሕወሓት ኣመራሮች እጅግ ኣስደንጋጭ ኣጋጣሚዎች ተፈጥረውባቸውል፤ ለያይተነዋል እናጫርሰዋለን ያሉት ሕዝብ ኣንድነቱን በኣደባባይ ኣሳይቷቸዋል፤ ይህ ያስብረገጋቸው ሕወሓቶች ድርድር ከኦሮሞ ተቃውሞ መሪዎች ጋር መጀመራቸው ይታወቃል።
ሕወሓት የራሱ የማዘናጊያ ስልቱን ተጠቅሞ የኦሮሞን ሕዝብ ትግል ለመግደል የጀመረው ድርድር እንዲሰምርለትና ኣዘናግቶ የተነሳውን ተቃውሞ ኣፈር ለማስበላት በካድሬዎቹ በኩል የኦሮሞን ሕዝብ ትግል ህገ መንግሥታዊ ነው፣ሁላችንም ልንደግፈው ይገባል በማለት የመደለያ እሾሃማ ቃላቶቹን እየረጨ ሲሆ በሕዝብ መካከል የሚኦር ኣንድነት ለማክሸፍ ሴራዎቹን በማስፋት ፕሮፓጋንዳ ተጠምዶ ስላሚገኝ ሁላችንም ይህንን እባብ የሕወሓት ኣገዛዝ በቃኽን ብለን እንደጀመርነው ልናስወግደው ይገባል።ትግሉ ይቀጥላል!!!! 
Image may contain: 3 people , text

No comments:

Post a Comment