ኢትዮጵያውያን ለነጻነታችን ዋጋ መክፈል የጀመርነው ከጥንት ጀምሮ መሆኑ ይታወቃል::በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ የሚገኘው የዘረኛ ቡድናዊ አገዛዝ በዜጎች ላይ ከፍተኛ በደል በማድረስ ላይ ይገኛል::ከዚህ ጨቋኝ አገዛዝ ለመገላገል ለነጻነታችን መታገል ያለብን እኛው ራሳችን እንጂ ምእራባውያን አይደሉም::ምእራባውያን ብሄራዊ ጥቅማቸውን የሚያስከብርላቸው ማንኛውም አስተዳደር ከመደገፍ እና ከማባበል ወደኋላ አይሉም::አምባገነኖች በምእራባውያን እየተረዱ በዜጎቻቸው ላይ የሚያደርሱት በደል እና ሰቆቃን ለመቃወም ከወረቀት ያልዘለለ ተግባር በለጋሽ አገሮች ሲፈጸም አልታየም::ለዚህ ጭቆና ችግሩም መፍትሄዉን የተጨቆነው ማህበረሰብ እንደሆነ ማወቅ ግድ ይላል::ነጻነቱን ለማግኘት የሚታገለው ጭቁን ሕዝብ በትግሉ ገፍቶ ሲራመድ ምእራባውያን ከአምባገነኖች ወደ ነጻነት ታጋዮች ፊታቸውን እንዲያዞሩ ይገደዳሉ::ለለጋሽ አገሮች ቅርብ የሆኑ ዲፕሎማቶች ተቃዋሚዎች ያላቸውን ሃይል አሰባስበው በተገኘው መንገድ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እስካላደረጉ ድረስ በውጪም በውስጥም ያሉትን ለመርዳት እና ለማበረታታት ከብሄራዊ ጥቅም አንጻር እንደማይቻል ከዚህ ቀደም አስረግጠው ተናግረዋል::
ምእራባውያኑ ከአፍ ወሬ ውጪ ምንም የሚተገብሩት ነገር የለም ፡ በእስር ቤት ያሉ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች በቂ ምሳሌ ሊሆኑ ይችላል ከሰብአዊ መብት ድርጅቶች ጀምሮ እስከ አሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚ/ር ድረስ ድምጻቸውን ቢያሰሙም ለይስሙላ እና ለብሄራዊ ጥቅማቸው እንዲሁም ነገ ሌላ መንግስት ቢተካ እንዲህ ብለው ነበር እንዲባልላቸው እና እዳ ማውረጃ ንግግራቸው ለትግሉ ምንምየሚፈይደው ነገር የለም።በእስር ለሚማቅቁት ወገኖቻችን የሚፈይደው ዋናውና አንዱ ጉዳይ የኛ ጠንክረን መታገል እና አንድ እርምጃ መጓዝ ሲሆን የዛን ሰአት የኛን መጠናከር እና መታገል የተመለከቱ ምእራባውያን ምን እንርዳችሁ ከምን ደረሳችሁ ምናምን ማለታቸው እና መጠየቃቸው ግድ የሚልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ፡፤ አሁን የሚፈለገው የኛ መታገል እና መታገል ብቻ ነው። የነጮቹ የከንፈር ልብላቤ ከብሄራዊ ጥቅም ሚዛን ሂደት ምስረታ ላይ ስለተመረኮዘ ከንግግር ውጪ ምንም አይፈይድም::
ከማእከላዊ አፍሪካ እስከ አፍጋኒስታን ከሶርያ እስከ ኢራቅ በተለያዩ የአፍሪካ እና የመካከለኛው እንዲሁም የኢስያ ሃገራት ም እራባውያኑ የሚያካሂዱት የፕሮክሲ ጦርነት የተነሳ ሌላ ዙር ቀውስ በምስራቅ አፍሪካ እና ውጥረት እንዲከሰት ስለማይፈልጉ ከወያኔ ጋር እጅና ጓንት ሆነው ለመስራት አለመቦዘናቸው የሚያመለክተው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃገራት ላይ በአሁኑ ሰአት ሊፈጠር የሚችለውን አመጽ እና ችግር መቆጣጠር ይዞ የሚመጣውን ውጤት እርግጠኛ ሆነው ለማወቅ አለመቻላቸው ከወያኔ ጋር እንዲተሳሰሩ አድርጓቸዋል።እንዲሁም ደቡብ ሶማሊያ ላይ ነዳጅ መኖሩን ስካን አድርገው ስላረጋገጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ25 አመት በኋላ እንግሊዝ ኤምባሲዋን ሞቃዲሾ የከፈተች ሲሆን ይህን ተከትሎ ከ100 በላይ የብሪታንያ ካምፓኒዎች ካልተረጋጋችው ሶማሊያ ፍቃድ እንደተሰጣቸው ለማረጋገጥ ተችሏል። ይህንን ከሶማሊያ ሊያገኙትን ብሄራዊ ጥቅም ሊያስጠብቅ የሚችለው አገር ቢኖር ወታደሮቹን ለሞት እየገበረ የሚተባበራቸው የወያኔው መንግስት ብቻ ስለሆነ ያላቸውን ሃይል ሁሉ በመጠቀም ሕዝብን በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ በመደለል የአምባገነኖች እድሜ እንዲረዝም ሚናቸውን ይጫወታሉ።
እንዲሁም ታጥቀናል እንዋጋለን ስለሚሉ ድርጅቶች እንቅስቃሴ በቂ መረጃ ስለሌላቸው እንዲሁም እነሱ የማይደግፉት እና የማይቆጣጠሩት አመጽ ላይ ሪስክ/ሃላፊነት ስለማይወስዱ የሚያደርጉል አስታውጾ አነስተኛ ሲሆን እኛ ታግለን አንድደርምጃ ወደፊት እስካልሄድን ድረስ እና ትግላችንን አሳይደን የድጋፍ እና የቁጥጥር ሰንሰሎችን ከም እራባውያን ጋር እስካልፈጠርን ድረስ በመግለጫ እና ድህረገጽ ወሬ ጋጋታ ምንም የምናመጣው ነገር እንዳሌለ ለመናገር እወዳለሁ፡፤ ዋናው ቁም ነገሩ ግን ጠንክረን የዲፕሎማሲውን እና የትጥቁን ትግል እና የሃገር ቤቱን ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ ከየኣቅጣጫው የፈጠረውን ንቅናቄ ትግል ከያዝነው ወያኔ ፈንግሎ ለመጣል በፍጹም ኣይቸግርም።
ብቸኛው እና ዋናው ጉዳይ ትግሉ\ጦርነቱ በመሃል እና በዳር አገር ከተፋፋመ ፣ ሕወሓት እና አመራሩ አደጋ ውስጥ መግባት ሲለጀመሩ ምእራባውያኑ በሌላው አለም እንደለመዱት ድርድር መግባባት ጉባዬ ወዘተ የሚባለዉን እንደ ጆከር ካርድ ስለጀመሩ መግባባት በማለት የመጀመሪያ እርከን የሆነውን የመግባቢያ ምስጢራዊ ድርድር ኣስጀምረዋል።
ወያኔ ያሰራቸውን የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች የተወሰኑትን እንዲፈታ ተደርጎ ድርድር እንዲጀመር ያደርጋሉ ከዚህ ውጭ ግን የሃይል ሚዛኑ በወያኔ እጅ ባለበት የመንግስትን ወንበር ተቃዋሚዎች ባላዩበት ሁኔታ ምእራባውያኑ የሚያሰሉት ከወያኔ ጋር ያላቸውን ቁርኝት ነው። ይህንን ለመበጠስ ደሞ የግዴታ የተኩስ ትግል መጀመር አለበት ። ወያኔም ቢሆን የትጥቅ ትግሉ በመሃል አገር እና በዳር አገር ሲስፋፋበት ጭንቀት ውስጥ ስለሚገባ ከአጣብቂኙ ለመውጣት ሲል ያለውን አማራጭ ለመጠቀም ይሞክራል። ወያኔ ደጋፊዎቹን እና ካድሬዎቹን በጥቅም ስለገዛቸው ጦርነት ከተስፋፋበት ያለውን ሃይል ሁሉ ወደ ዛው ስለሚያጋድለው ለካድሪዎቹ ጥቅሞች ጊዜ ስለማይኖረው አብዮታዊ መበላላት በፓርቲው ውስጥ ስለሚፈጠር እድሜውን ማቀጨጭ ከዛም መጣል ይቻላል። ጠንክረን በሃገራዊ የጋራ አጀንዳችን እና የህዝብን ነጻነት በማረጋገጥ ላይ አስረግጠን መታገል ካልቻልን ባሁኑ በተገኘው ነገር ላይ ሁሉ ተስፋ በመጣል አካሄዳችን ወያኔን እንድማንጥለው ማወቅ አለብን። ምእራባውያኑም የኛን መጠናከር ሲያዩ የዛኔ ይፈልጉናል፥፤አትኩሮታችንን ሁሉ በትግሉ ላይ የማድረግ ግዴታ አለብን።#ምንሊክሳልሳዊ
No comments:
Post a Comment