ነገ ቅዳሜ ነሐሴ 7 የሚደረጉ ሰልፎች አይኖሩም። በጎጃም፣ በወሎችም በሽዋ ሰልፎቹ የሚደረጉት እሁድ ነሐሴ 8 ቀን 2008 ዓ.ም ነው። በደሴ፣ በወልዲያ፣ በኮምቦልቻ፣ በደብረ ብርሃኑ፣ በከሚሴ፣ በሸኖ፣ በደብረ ማርቆስ፣ በቢቸና …….እያለ ይቀጥላል።
በጎጃም ሰልፎቹ ይደረጋሉ ተብሎ ከአንድ ሳምንት በፊት የተነገረው ቅዳሜ ቢሆንም፣ የሰልፉ አስተባባሪዎች የአገዛዙን ሃይል ለመበታተን በሚልና ሌሎች የሎጂስቲክ ምክንያቶች የጎጃሙን ሰልፍ በአንድ ቀን መሆኑ ላለፉት 5፣4፣ ቀናት ሲያስተዋወቁ ቆይተዋል።
ሆኖም ግን የሕዝብ የከፋ እንደመሆኑና ሕዝቡ ለትግል ከመቼዉም ጊዜ በላይ በመነሳሳቱ በማናቸውም ሰዓትና ቦታ የሚገነፍል ነገር ሊኖር እንደሚችል ግን የሚታወቅ ነው።
ወያኔዎች የማሰርና የማስፈራራትተግባራትን እየፈጸሙ ቢሆንም ከገጠር አካባቢዎች ሁሉ ሰዉ ወደ ከተሞች ገብቶ እያደረ ነው።
ድለ ለኢትዮጵያ ህዝብ
No comments:
Post a Comment