Saturday, August 13, 2016

ከሰልፉ በኋላ በደብረ ማርቆስ ቀበሌ 03 ጽ/ቤት ወጣቶች በገፍ ታስረዋል


ከሰልፉ በኋላ በደብረ ማርቆስ ቀበሌ 03 ጽ/ቤት ወጣቶች በገፍ ታስረዋል:: የደብረማርቆስ ወጣቶች በአምባገነኑ አጋዚ ወታደሮች ቤት ለቤት እየታፈኑ በጭካኔ እየተደበደቡ ነው።

ዛሬ ረፋድ ላይ የተጀመረው የደብረ ማርቆስ ዐማሮች የተጋድሎ ሰልፍ አሁን 10 00 (Time) ላይ ተበትኗል፡፡ ከሦስት የተለያዩ አቅጣጫዎች የተጀመረው የተጋድሎ ሰልፍ ወደ አንድ ቦታ ማዕከል እንዳይገናኙ የአጋዚ ወታደሮች በጥይት ተከላክለዋል፡፡ ሰልፉ በአብማ (ቀበሌ)፣ በሸዋ በር (ቀበሌ 06) እና መናሃሪያ አካባቢ የተጀመረው የተጋድሎ ሰልፍ በዐማራው ሕዝብ ላይ እየደረሱ ያሉ በደሎች ተስተጋብተዋል፡፡ ‹‹ወልቃይት የዐማራ ነው፤ ፖሊስ የሕዝብ ነው›› የሚሉት መፈክሮች ጎልተው ይሰሙ ከነበሩት ቀዳሚዎቹ ነበሩ፡፡
የዐማራ ፖሊስ ምንም ዓይነት እርምጃ ያልወሰደ ሲሆን የአጋዚ ጦር ግን በንጹሐን ዐማሮች ላይ ጥይት አርከፍክፏል፤ ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች ቆስለዋል፤ በሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንዳለ ሰምተናል፡፡ አሁን ላይ ብረት ለበስ የመከላካያ ሠራዊት የንጉሥ ተክለ ሃይማኖት አደባባይን ወሮታል፡፡ ከመንገድ ወደ መንገድ ሰው መንቀሳቀስም እንደተገደበ ነው ከቦታው የደረሰን መረጃ የሚያመለክተው፡፡

አሁን ላይ ከመቶ የሚበልጡ ወጣቶች የፖሊስ ጣቢያዎች በመሙላታቸው ምክንያት በቀበሌ 03 ጽ/ቤት ውስጥ ታጉረው እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ በርካታ ልጆች ተደብድበዋል፡፡ የአባቶቹን ሰንደቅ ዓላማ ለብሦ የነበረ ኃይለኛው የተባለ ወጣት ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶበታልም ተብለናል፡፡
በደብረ ማርቆስ ከተማ የነበረው የዐማራ ተጋድሎ ሰልፍን በተመለከተ የተለያዩ አካላት የተለያየ መረጃ ማስተላለፋቸው በደብረ ማርቆስን ዐማሮች ውዥንብር ፈጥሮ ተስተውሏል፡፡ በመሠረቱ የትግሉ ባለቤት ራሱ ሕዝቡ ሆኖ የሕዝቡን መርሃ ግብር ማስተጋባት የተሻለ ቢሆንም የተለያዩ አካላት በራሳቸው መንገድ ፕሮግራሙን ማስተዋወቃቸው የዐማራው ትግል ላይ አሉታዊ ተጽእኖ አሳድሯል፡፡

ከደብረ ማርቆስ ከተማ ያነጋገርናቸው ሰዎች ወጣቶቻችን የሚታፈኑት በማኅበራዊ ሚዲያ በሚወጡ ምስሎች በመሆኑ ምስሎቹን ሰዎቹ በማይታዩበት መልኩ እንዲሆንም አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

No comments:

Post a Comment