ከዚህ በታች ያለውን ለማሰራት ከአርባ ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ተደርጓል። የሕወሃት ተላላኪ ሙክታር ከድር ነው በቦታዉ ሄዶ ያስመረቀው። ዶር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ በመጽሃፋቸው እንደገለጹት ፣ ሕወሃት፣ ኦህዴድን አዞ ይሄን ሃዉልት ያሰራበት ታሪክ, ምንም አይነት የጽሁፍ ማስረጃ የሌለበት አፈታሪክ ብቻ ሳይሆን ዉሸትም እንደሆነ ነ ያስቀመጡት።
እንግዲህ ሕወሃት ዉሸትን እየፈጠረ ( እንደ ተስፋዬ ገብረ አብ ያሉትን በመጠቀም) ነው በአማራኛ ተናጋሪዎች እና በኦሮሞኛ ተናጋሪዎች መካከል መቃቃር እንዲኖር ለማድረግ ነው የሞከረው።
ምን ችግር ነበረው ይሄንን የጥላቻ ሃዉልት ከሚሰሩ፣ ክሊኒክ፣ ትምህርት ቤት የመሳሰሉት እዚያ አካባቢ ላለው ማህብረሰብ ቢሰሩበት ? እዚህ ሃዉልት ይሰራ ከተባለ ደግሞ በገዳ ስርዓት ጊዜ መቼም ጀብሩ የፈጸሙ ታላላቅ የኦሮሞ አባቶች ይኖራሉ። ሌላውም ከታሪክ እንዲማር፣ የበለጠ ስለ ኦሮሞ ባህል እንዲያወቅ፣ የአንዳቸውን ሃዉል ለምን አያቆሙም ?
ይህ ሃዉልት የተሰራው ሊከፋፍለን፣ ሊያጣላን ነው። ጎንደር እና ጎጃም “የኦሮሞዎች ደም የኛ ደም ነው” ሲሉ ነበር። ኦሮሞዎች በአዳማ “አማራ የኛ ነው” እያሉ ነው። ከዚህ በኋላ አንፈራራም። ከዚህ በኋላ አማርኛም እንማራለን፣ አፋን ኦሮሞም እንማራለን። አማርኛም የኛ ነው፤ አፋን ኦሮሞም የኛ ነው። ሁለቱንም እንይዛለን። በቋንቋ አንከፋፈልም።
የተማረ ይግደለኝ ነው የሚባለው። እናመሰግናለን ዶር ፍቅሬ ፣ ታላቅ የኦሮሞ ልጅ፣ የኢትዮጵያ ልጅ …
“የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ”
ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ
ገፅ ፡152-153
ገፅ ፡152-153
“አፄ ምኒልክ ደም መፈሰስን እናስቀር ብለው ንጉሥ ጦናን ለመኑት።ንጉሥ ጦና ግን ኃይሉን አሟጦ መዋጋት ስለመረጠ በምኒልክ ሠራዊት ላይ ከባድ ጉዳት አደረሰ። በመጨረሻ ግን ቆሰለና ተማረከ።ዳግማዊ ምኒልክ ጦናን አይቀጡ ቅጣት ከመቅጣትና መንግስቱንም አሽቀንጥረው ጥለው ሥልጣኑን ለጦር መሪዎቻቸው ከመስጠት ይልቅ ደግነት የተሞላበት ምህረት አድርገውለት እንደሚገብርላቸው ቃል ካስገቡት በኃላ ወደ ሥልጣኑ መለሱት። ምኒልክ ተበቃይ አልነበሩም ።ይቅር በይ፣ በተጨባጭ እውነታ ላይ የተመሰረተ ምክንያታዊ አስተሳሰብ የነበራቸው እና ራሳቸውን እነደ ጥሩ ክርስቲያን የሚያዩ ሰው ነበሩ።በጦርነት ላይ የሴት ልጅ ጡት መቁረጥ ፍጹም ከባሕሪያቸው ውጪ ነው።እንዲህ ዓይነቱ ውንጀላ መሰረተ―ቢስ እና ከተንኮለኞች የመነጨ ነው።የጎጃሙ ንጉሥ ተክለሃይማኖት አምጸው ጦርነት አነሱና ቆስለው ተማረኩ።ምኒልክ የቆሰለውን ምርኮኛ ገድሎ በመጨረስ ፈንታ ቁስላቸውን ራሳቸው አክመው ፣አጠገባቸው አስቀምጠው አብረዋቸው እንዲመገቡ በማድረግ ፍቅር ነው ያሳዪአቸው።ሥልጣናቸውንም አልወሰዱባቸው፤ ያለማመንታት መልሰውላቸዋል። በርግጥ ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ሩኅሩኅ ነበሩ።አገራቸውን ለመውረር የመጡ ምርኮኞች ጣልያኖችን እንኳ በርኅራኄና በደግ አያያዝ ነበር የያዟቸው።እኝህን ሰው ጡት ቆርጠዋል/አስቆርጠዋል/ ብሎ መፈረጅ አግባብነት የሌለው ትንሽ የፓለቲካ ጠቀሜታ ለማግኘት የሚነዛ ርካሽ ፕሮፓጋንዳ ነው።ምኒልክን ጡት ቆርጠዋል ብለው ለማስጠላት ሀውልት ያቆሙ አካላት በድርጊታቸው ማፈር እና ያንን አሳፋሪ ሀውልትም ማፍረስ ይገባቸዋል። ምኒልክ በግላቸው እንደዚያ ዓይነት ተግባር ጨርሶ አይፈጽሙም።”
No comments:
Post a Comment