ቀብራራውና ኩሩው የሸዋ ህዝብና የሸዋ ምድር ጀግና አጥቶ አያውቅም የሩቁን ጊዜ እንኳን ረስተን ከጥቂት አመታት በፊት ስለነበረው የሸዋው ጀግና ላጫውትህ ይህ ሠው ጀግና ካልተባለ ማንም ጀግና ሊባል አይገባውም። የፈፀመው ገድል ለአንባቢ እንኳን አፈታሪክ እስኪመስል ለማመን የሚከብድ ነው። እኔ በግሌ ኢትዮጵያ ስለዚህ ሰው የጀግንነት ተጋድሎ ሳወራም ሆነ ስፅፍ ውስጤን ይሞቀኛል። ጀ..ግ… ና ብዬዋለሁ ይህንን ሰው አስማረ ዳኜን።አስማረ ከደርግ ስርአት ጀምሮ በሽፍትነት የኖረ የጫካን ሕይወት ጠንቅቆ የተረዳ የህዝቡን በደል በሚገባ የሚያውቅ ታላቅ ጀግና ነው አስማረ ዳኜ።ይህ ጀግና አስማረ በ1983 አመተ ምህረት በአርባጉጉ ይኖሩ የነበሩ የአማራው ጎሳ ተወላጆች ላይ በኢሕአዴግ እና በኦነግ ወታደሮች እየደረሰ በነበረው ጭፍጨፋ ልቡ አዝኖ በሰሜን ሸዋ ጊናገር የሚገኙ 15 ገበሬዎችን በማስተባበር ምስራቅ ኢትዮጵያ አርባጉጉ ድረስ በመጓዝ በአካባቢው በሚገኙ የኦነግና የኢህአዴግ ወታደሮች ላይ ጥቃት በመክፈት የኦነግና የኢህአዴግ ወታደሮችን ውሀ ውሃ አሰኝቶ በአርባጉጉ የሚገኙ የአማራው ጎሳ አባላትን እልቂት የቀነሰ ታላቅ በስፍራው ይገኙ የነበሩ ሕዝቦች ባለውለታ ነው።የአስማረ ዳኜን ጀግንነት የተረዱት የወቅቱ የኢህአዴግ ሹማምንት አስማረ የኦነግና የኢሕአዴግ ሠራዊትን አርባጉጉ ላይ ድባቅ መቶ ሲመለስ ሰሜን ሸዋ ላይ በመጠበቅ አማላጅ ልከው የጊናገር ወረዳ አስተዳዳሪ እንዲሆን አደረጉት ሆኖም አስማረ የጊናገር ወረዳ አስተዳዳሪ ሲሆን በልቡ መላ ዘይዶ ነበር።አስማረ ዳኜ የጊናገር ወረዳ አስተዳዳሪ ሆኖ በተሾመ በጥቂት ወራት ውስጥ በወረዳው የሚገኘውን የመሣሪያ መጋዘን በመስበር መሳሪያውን ለሰሜን ሸዋ የአማራ ገበሬዎች እና በከሰም ወንዝ አቅራቢያ ለሚገኙት የአፋር አርብቶ አደሮች በማከፋፈል የአካባቢውን ገበሬ አስከትሎ ዳግም ሰሜን ሸዋና አካባቢውን ከኢህአዴግ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት ተመልሶ ወዳደገበት ጫካ ተመልሶ አስግሮት የተሰኘ አካባቢ በመመሸግ ህዝቡን ነጻ ለማውጣት መሸፈቱን ለኢህአዴግ ሹማምንቶች መልእክት ላከ።በአስማረ ዳኜ ድርጊት የተበሳጩት የኢህአዴግ ሹማምንቶች ሁለት ብርጌድ ጦር ወደጊናገር በመላክ በአስማረ ጦር ላይ ቀጥተኛ ጦርነት ከፈተ ሆኖም የአስማረ ጦር በቀላሉ ሊበገር አልቻለም ምክንያቱም ሰውዬው አስማረ ዳኜ ነው ይልቁንስ በአስማረ ይመራ የነበረው የገበሬዎች ጦር ጠላትን በሞት መሬት ውስጥ በመክተትና ቆርጦ በመምታት በአንድ ቀን ውጊያ ብቻ በርካታ ወታደሮችን ሲገድሉ አምስት ወታደሮችን ከነሙሉ ትጥቃቸው ማረኩ። በዚህ የአስማረ ጦር ጀግንነት የተበሳጩት የመንግሥት ሹማምንት በሄሊኮፕተር የታገዘ ጥቃት በአስማረ ጦር ላይ ቢከፍቱም አስማረ አልሸሸም ወይ ፍንክች የአባ ቢላዋ ልጅ
በአካባቢው በኢህአዴግ ጦር በአስማረ ጦር የተካሄደው ጦርነት በአስማረ አሸናፊነት መጠናቀቁ እልህ ውስጥ የከተታቸው የገዢው ፓርቲ ሹማምንት አስማረን ለመግደል ሰላዮችን ወደጊናገር ወረዳ ይልካሉ ሆኖም አስማረ ሰላዮችን እና አብረው የመጡ ወታደሮችን ቀድሞ በመመልከት ተኩስ ከፍቶ ሁለቱን ገድሎ አምስቱን ይማርካቸዋል የተማረኩትን ጊናገር ገበያ ላይ አስሯቸው ስለነበር ወታደሮቹን ህዝቡ እየተመለከተ የአስማረ ምርኮኞች እያለ ይሳለቅባቸው ነበር።ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ የአስማረ ጦር ካለው የበጀት እጥረት የተነሣ ችግር እንደሚገጥመው የተረዳው አስማረ ጦሩን አስከትሎ ከማንም በላይ ወደሚወዳቸው እና ወደሚያምናቸው አፋሮች ዘንድ ተጓዘ። በነገራችን ላይ አስማረ ለአፋሮች የነበረው ፍቅር አፋሮችም ለአስማረ የነበራቸው ፍቅር ልዩነት ነው። እኔ እንኳን ከዚህ በፊት የአስማረን ገድል ስጽፍ የአፋር ክልል ተወላጅ የሆኑ ወዳጆቼ አስማረን አንስተህ አፋርን መተው ጥቁር ድመትን በጨለማ እንደመፈለግ የማይታሰብ ነውና አፋር የአስማረ ውለታ አስማረም የአፋር ውለታ አለባቸው።አስማረ ዳኜ ከአርጎባ መንደር በደረሰ በ3ኛው ቀን የኢህአዴግ ሠራዊት የአስማረን በአካባቢው መኖር ሰምተው በከባድ መሣሪያ የታጀበ ጦርነት በአካባቢው ላይ ይከፍታሉ ሆኖም አስማረ ከሰሜን ሸዋ አብረውት በመጡት ገበሬዎች እና የአፋር ወዳጆቹ ድጋፍ በስፍራው የሚገኘውን የኢህአዴግ ጦር ይደመስሳል በድሉ የልብ ልብ የተሰማው አስማረ ከሰሜን ሸዋ አብረውት ከመጡት ወታደሮቹ መካከል ሁለቱን አስከትሎ ለወታደሮቹ ቀለብ ለማምጣት መተሐራ ወደሚገኘው ተወካዩ ዘንድ ይሄዳል። ሆኖም የመተሐራው ተወካይ ለገንዘብ ብሎ በኢህአዴግ መገዛቱን በአፋሮች የወሬ ቅብብል ባህል ዳጉ አማካኝነት ይሰማል በዚህም የተነሳ መንገዱን በመቀየር በከሰም በኩል በማድረግ ሽሬ የምትባል የገጠር መንደር እረፍት ወስዶ ካሰበበት በኋላ ወደስፍራው በመሄድ ከመተሀራው ተወካዩ ጋር በተቃራኒ አቅጣጫ መሽጐ ሁኔታዎችን መከታተል ይጀምራል በዚህም የመተሀራው ተወካይ ለማስመሰል ቀለብ በመኪና ጭኖ ከፊት ሲሄድ በሌላ በኩል በርካታ ወታደሮች የጫነ መኪና ሲመጣ ተመልክቶ ቀድሞ ተኩስ ከፍቶ አንድ በአንድ ይለቅማቸዋል ሆኖም የተኩስ ድምፅ የሰማው አንድ ብርጌድ የኢህአዴግ ሠራዊት በስፍራው በመድረስ በአስማረ እና በሁለቱ ጓደኞቹ ላይ ተኩስ ይከፍታሉ ከዚህች ክስተት በኋላ የአስማረ መጨረሻ ሊታወቅ አልቻለን። የኢህአዴግ ወታደሮች ሁለት ሹሩባ የተሰሩ ወጣቶች አንገትን በመቁረጥ በሰሜን ሸዋ እየዞሩ “አስማረን ገድለነዋል ይሄው ጭንቅላቱ” በማለት ለሕዝቡ ያሳዩ ቢሆንም ህዝቡ ተቆርጦ የተያዘው ጭንቅላት የአስማረ አለመሆኑን መግለጻቸውን በስፍራው የነበሩ የአካባቢው ተወላጆች አጫውተውኛል የነፀብራቅ መጽሐፍ ደራሲ አቶ አሰግድ መኮንን የተለየ ነገር ካለ ብዬ በስልክ አዋርቼው ነበረ ሆኖም እርሱም አስማረ ስለመሞቱ እርግጠኛ መሆን እንደማይቻል አጫውተውኛል።
ታድያስ ይህንን የመሳሰሉ ጀግኖችን ያፈራው የሰሜን ሸዋ ህዝብ ዛሬ እንደጀግና አልባ በቀዬው በመንደሩ ስደተኛ አባቶቹ ባስከበሩት መሬት ላይ እንደምንስ ባሪያ ሆኖ ይኖራል፡፡ ታላቁ የሸዋ ህዝብ ሆይ ስለታሪክህና ስለነገው ልጆችህ ስትል ወያኔን ከሰሜን ሸዋ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማባረር ህብረት ፈጥረህ ያንን ጠንካራ ጡቻህን ለኢህአዴግ ሹመኞች አሳያቸው የአማራውና የኦሮሞው ግድያ ይብቃ በላቸው፡፡
ጃሎ በል
አልበለጥም አልበለጥም
የአስማረ ዘር ነኝ ያውም ኢትዮጵያዊ እጄን አልሰጥም
ብለህ አቅራራባቸው
#ኤርሚያስ_ቶኩማ

No comments:
Post a Comment