ዛሬ በባህር ዳር ይደረጋል የተባለው ሰልፍ ሳይደረግ ቀርቷል። ሰልፉ አቶ በረከት ስሞን ትላንት በጎንደር ያደረጉትን አይነት (ወጣቶች በድንጋይ አዳራሹን የደበደቡበት) በባህርዳር ለማድረግ አስበው ስለነበረ፣ ያንን በመቃወም የነበረ ሲሆን፣ አቶ በረከትም ሰልፍ እንዳይቀሰቀስ በመስጋት፣ የባህር ዳር ጉዟቸዉን ሰርዘው፣ በድጋሚ ትላንት ያልተሳካዉን ስብሰባ ከተወሰኑ የአገር ሽማግሌዎች ጋር በጎንደር አድርገዋል።
በጎንደር ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ከሽማግሌዎች ጋር በተደረገው ስብሰባ የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ በአስቸኳይ መፍትሄ እንደሚያገኝና የታሰሩ የኮሚቴ አባላት ያለ ቅድመ ሁኔታ በአሰቸኳይ እንደሚፈቱ ቃል ገብተዋል። ሽማግሌዎቹ “እስካሁን ድረስ ብዙ ጊዜ ቃል ገብታችሁ ቃላችሁን በልታችኋል፤ ስለዚህ ልናምናችሁ አንችልም፤ ሆኖም በተሎ መልስ ብትሰጡን አገሪቱ እያጋጠማት ያለውን ቀውስ መቀነስ ትችሉ ነበር፡፡ እኛ ግን መልስ እስኪሰጠን ድረስ መቼም ቢሆን ትግላችን አናቆምም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
በተያያዘ ዜና በጎንደር እና በባህር ዳር ከተማ ቁጥራቸው እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆኑ ወጣቶችን የአጋዚ ወታደሮች አፍሰው እያሰሩ ሲሆን፣ ያሉ እስር ቤቶች በሙሉ ከመሞላታቸው የተነሳ ትምህርት ቤቶች ሳይቀሩ እንደ እስር ቤት እያገለገሉ ነው። ወጣቶቹ በእስር ቤት ሆነው መፈክሮችን እያሰሙ የአገር ዘፈኖችን እየዘፈኑ የበለጠ የመመካከሪያ፣ የመደራጃና የመወያያ ቦታም እያደርጓቸው እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በመታፈሳቸው እንኳን ሊደነግጡ መታፈሳቸዉን እንድ ክብር እየቆጠሩት ነው።
በጎንደርም በባህር ዳር፣ ስራ፣ ንግድና ማናቸውም አይነት እንቅስቃሴ የሌለ ሲሆን አገዛዙ ለጊዜው ወጣቶችን በጅምላ አፍሶ፣ ከሽማግሌዎች ጋር ተናጋግሮ ሁኔታዎችን ለማርገብ በጣም ደፋ ቀና እያለ ነው። ከሕዝቡ ጋር ስምምነት ከሌለ ወደ ባሰ አዘቅት ዉስጥ እንደሚገባ የተረዱት ገዢዎች በከፍተኛ ደረጃ፣ ጳጳሱን ከፊት ከማስቀደምና በቴሌቭዥን ከማቅረብ ጀምሮ፣ የእምነት አባቶችን እያሰማሩ፣ ታቦት ይዘው እየሄዱ “ለህዝቡ ትለል ተስፋ በመስጠት፣ ችግሮች ይፈታሉ፣ እንወያይ፣ ሰዉን አረጋጉልን” እያሉ ነው።
ሕወሃቶች ፣ በጋይንት ሕዝቡን ለማባባል፣ ታቦት ይዛቹህ ውጡ የተባሉ አባት እምቢ ስላሉ ቄሱን በመግደል አንድ ወታደር የቄሱን ልብስ ለብሶ ታቦት እንዲሸከም አድርገው መውጣታቸውን የሰሙ የህዝብ ታጣቂዎች፣ ታቦት የተሸከመውን ወታደር እግሩን አልሞ በመተኮስ የቆረጡት ሲሆን፣ ሌሎች ቄሶችም ታቦቱን በክብር አንስተው ወደ ቤተክርስቲያን አስገብተውታል።ያን ያህል እምነተ ቢስ የሆኑ ህወሃቶች ሕዝብ በነርሱ ላይ ያለውን ተቃዉሞ ለጊዜው ላማለዘብ ሲሉ ታቦትን እስከመድፈር ድረስ የደረሱበት ሁኔታ ነው ያለው፤፡
በአርማጭሆ ታግተው የነበሩ 3 ኦራል ሙሉ ወታደር በድርድርና በቄሶች ምላጃ፣ ባዶ እጃቸውን ተለቀዋል።መሳሪያቸውን ሙሉ ለሙሉ የአካባቢው ሰው ወስዷል። ከሽምግልናው በተጨማሪ የተማረከ ወታደር ያውም መሳሪያውን የተቀማ መግደል የአርማጭሁ ህዝብ ባህል ስላልሆነም ነው ወታደሮች በነሳ የተለቀቁት። በአካባቢ በተደረጉ ጦርነቶች ከመቶ በላይ ወታደሮች እንደተገደሉና አሁንም አልጋ ላይ ያሉ፣ ጭራሹኑ አካለ ጎዶሎ የሆኑ ብንዙ እንዳሉም ይነገራል።
ግርማ ካሳ
No comments:
Post a Comment