Sunday, August 14, 2016

የአማራ ክልል በወያኔ ጦር ሰራዊት ተወሯል


በሰሜን ሸዋ ሸዋ ሮቢት እና አካባቢዋ እንዲሁም በኤፍራታና ግድም ወረዳ፡ በቀወት ወረዳ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እየተዘጋጁ ባሉበት ሁኔታ አጠቃላይ የፀጥታ መዋቅሩ ከዞን በመጡ ከፍተኛ አመራሮች ሰሞኑን በሸዋ ሮቢት ከተማ እና በአጣዮ ከተማ/ ኤፍራታና ግድም ወረዳ/ ዉስጥ ስብሰባ ካደረጉ በሁዋላ ለፀጥታ መዋቅሩ በከተማው እና በገጠር አካባቢ ስምሪት ተሰጠ ። በዚህም መሰረት ቤት ለቤት እየዞሩ ሁሉም ከቤታቸው እንዳይወጡ ትእዛዝ እየተሰጠ ሲሆን በነዚህ አካባቢዎች ማንኛውም ሰው ያለ መታወቂያ መሔድ የማይችል ሲሆን ሁሉም የታጠቁ የመንግስት ታጣቂ እና የግል ታጣቂዎች ከየቤታቸው የእየተወሰዱ በፀጥታ መስሪያ ቤት እንዲቀመጡ እየተደረገ ነው። ከሁለት ሰው በላይ አብሮ መጓዝ የለም። ከፍተኛ ድብደባ እየተደረገ ነው።
በትላንትናው እለት በሸዋ ሮቢት ቅዳሜ ገበያ ደምቆ የሚውል ቢሆንም ህዝቡ ገበያ እንዳይገበይ መንገዱ ላይ በፀጥታ ሀይል ያለ መታወቂያ ማለፍ አይችልም እየተባለ ተመልሰዋል። ገበያው ጭር ብሎ ዉሏል። ማንም ሰው፣ በተለይ የገጠር ነዋሪዎች ከተማ እንዳይገቡ መንገዶች በወያኔ ጦር ተዘጋግተዋል። የቀወት እና የኤፍራታና ግድም ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች ሁሉም የቢሮ ፀሀፊ ሳይቀ ከተማ ውስጥ መታየት የለበትም በሚል እና ሰላማዊ ሰልፍን ሊቀላቀል ይችላል በማለት ሁሉም መስክ በማለት ገጠር ለስራ ተብሎ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ስምሪት ተሰጥተዋል። በነዚህና በሌሎች በርካታ ስልታዊ መንገዶች ሰልፍን ለማስወገድ እየተደረገ ነው።
ጎንደር፣ ወሎ፣ ጎጃምና በአጠቃላይ የአማራው ክልል በተመሳሳይ ሁኔታ በወያኔ ሰራዊት ተወሯል። ህዝቡም ተቃውሞውን ቤት በመቀመጥ እየገለጸ ይገኛል።

No comments:

Post a Comment