Sunday, August 21, 2016

እየተተገበረ ያለው «የመለስ ራዕይ»


ከአቻምየለህ ታምሩ
እነሆ ያለውን አቅምና ጉልበት ሁሉ ሳይቆጥብ ለክፉ ተግባር ያዋለው፤ በእምነትና በቅን መንፈስ ተገፋፍቶ ያለፋቸው ክፉ ነገሮች በመብራት ተፈልገው የማይገኙበት፤ በትምህርት ተወልደው መልካም የሚሰሩና ለወገናቸው የሚያስቡ ሰዎችን በማጥፋት ክብረወሰን የተቀዳጀው፤ ድሀ ዘራፊና ገፋፊው፤ተራ ወንጀለኛና ጨካኝ አረመኔው መለስ ዜናዊ ከሞተ አራት አመታት አለፈው።
እሱ የገነባው የማፍያ ስርዓት ግን ወራሾቹ «የመለስ ራዕይ» ብለው በሚጠሩት የግለሰብ ቤት፤ የህዝቦችን የመኖር ህልዉናና ሀገር ከማፍረስ የዘለለ ፋይዳ በሌለው የጥፋት መመሪያ እየተገፋ ዛሬ ላይ ግማሽ ህይወቱ ወደ ሞት ተለውጦ እውር ድንብሩን እየሄደ ከሚገኝበት የፍጻሜው አጋማሽ ላይ ደርሷል።
ምድራዊ ገነትን ፈጥሮ የሰው ልጆች ከችግር፣ ከበሽታና ከድንቁርና ነጻ ወጥተው፤ ወንጀል፣ እስራት፣ ጭቆና፣ ግፍና የኑሮ ጭንቀት ተረስተው የሰው ልጆች በፍቅርና በደስታ እንዲኖሩ ለማድረግ መጣጣር የኛ ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለም ሕልም የሆነ ታላቅ ግብ ነው። ብዙ ሀገሮች ከዚህ ገነት በመጠኑ ቀረብ ብለው አሁንም እርምጃቸውን እያፋጠኑ ወደዚያው ጨርሶ ለመግባት በመገስገስ ላይ ናቸው። እየተተገበረ በሚገኝው «የመለስ ራዕይ» በምትገዘገወዋ የወያኔዋ ኢትዮጵያ የምንኖር እኛ ግን ከሁሉ በተለየ ሁናቴ ተፈርዶብን ከትግራይ በበቀሉ ጨካኝ አውሬዎች ምክንያት ከገነቱ ቀርቶ ከመካነ-ንስሐው ሳንደርስ ገና በሲኦል ውስጥ ሁነን ስንሠቃይ እንገኛለን።
በሥልጣኔ ወደፊት የገፉት አገሮች ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦችን ያየ ማንም ሰው እኛ እንደ ሰው ነው የምንኖረው ብሎ ማመን እጅግ ያስቸግረዋል። እኛ የምንኖረው የትግራይ ጨካኝ አውሬዎች ባበጁልን የቁም መቃብራችን ውስጥ ነው።
«የመለስ ራዕይ» እየተባለ የሚንቆለጳጰሰው የወያኔ ፕሮግራም ተልዕኮ አማራውን ከምድረ ገጽ በማጥፋት በመቃብሩ ላይ የትግራይን ሪፑብሊክ መመስረት ሲሆን የፕሮግራሙ ራዕይ ደግሞ ከመቶ አመታት በኋላ ዛሬ «ኢትዮጵያ» በምትባለው አገር ውስጥ የአማራ ህዝብ ሳይሆን የአማራ ህዝብ መቃብር ብቻ እንዲኖር መስራት ነው። የወያኔ ደዌ ተሸካሚዎች የሆኑ ሁሉም የተከዘ ማዶ ፖለቲከኞች ይህን የመለስ ራዕይ በቶሎ ተሳክቶ ማየት ይፈልጋሉ።
እየተተገበረ የሚገኝው «የመለስ ራዕይ» የተከዘ ማዶ ወርቆቹን «በኤፈርት የአምስት አመት የኢንዲስትሪ ልማት መርሀ ግብር» ፋብሪካ በፋብሪካ አድርጎ እኛን ከወርቅ በታች የሆነውን አፈሮች ደግሞ ርስ በርስ እያከሳከሰ በማጫረስ ከምድረ ገጽ እንድንጠፋና እነሱ በመቃብራችን ላይ ታላቋን የትግራይ ሪፑብሊክ እስኪገነቡ ድረስ ድኩማን፣ ለማኞች፣ ረኃብተኞችና ደንቆሮዎች ሆነን እንድንኖር የሚያስችል የነውረኞች ፕሮግራም ነው።
እየተተገበረ ያለው «የመለስ ራዕይ» ቀደምት አባቶቻችን ያቀኗትን አገር የአማራ የመቃብር ዋሻ በማድረግ ያ ራዕይ እውን እስኪሆን ድረስ ደግሞ ምድሪቱ የወርቆቹ ጨቋኞች፣ ዘራፊዎች፣ ቀማኞችና ወንጀለኞች አገር እንድትሆን የመሰረት ድንጋይ የጣለ ህገ አራዊት ነው።
እየተተገበረ ያለው «የመለስ ራዕይ» እኛን በጉድ አዘቅት ውስጥ ከተው እነሱ ግን «ዘራችን ከዘራቸው፤ ደማችን ከደማቸው ይበልጣል» ብለው ተከታዮቻቸውን ሲጠምቁ የኖሩት የትግራይ ጨካኝ አውሬዎች ለግል ጥቅማቸው ያቋቋሙትንና ህዝባችንን እየፈጁበትና ሀብቱንም እየበዘብዙበት እንዲኖሩ በወንጀል ያቋቋሙትን የሌብነትና የቅሚያ ማህበራቸው የሆነውን «ስመ መንግስት» የሚገዘግዙበት የዘረፋ አዋጅ ነው።
አማራ ሆይ! የነገ ሳይሆን የዛሬ የመጀመሪያው ተግባርህ የምትኖርበትን የቁም መቃብር መግነዝ ቀዳደህና በጣጥሰህ የተጫነብህን የመቃብር ድንጋይና አፈር ፈነቃቅለህ ከዳር ዳር በአንድነት የራስህን የጎበዝ አለቃ መርጠህ ካልተነሳህ ከትግራይ ሪፑብሊክ በመለስ ምንም ያልቀረበው እየተተገበረ ያለው የመለስ ራዕይ በመቃብርህ ላይ ሙሉ በሙሉ ሊፈጸም ጫፍ ደርሶልሀል!

No comments:

Post a Comment