Friday, August 5, 2016

በጎንደርና ኦሮሚያ የሚካሄዱትን ተቃውሞችን ለመግታት እርምጃ እንደሚወሰድ ጠ/ሚ ሃይለማሪያም ገለጹ


ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008)
በወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ሃዝባዊ መሰረት የሌለው ነው ሲሉ ከቀናት በፊት የገለጹት ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ፣  መንግስት ህግ የማስከበር ሃላፊነቱን ለመወጣት ህገወጥ ያለውን ድርጊት ለመግታት እርምጃን እንደሚወስድ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
የጎንደር ከተማ ተቃውሞ እየተካሄደ ባለበት ወቅት መግለጫን የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህዝቡ አሉ የሚላቸውን ችግሮች በዴሞክራሲያው መንገድ ለመፍታት የሚችልበት ሰፊ እድል አለ ሲሉ ተናግረዋል።
በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ያሉና በኦሮሚያ ክልል የተጠሩ ሰልፎች አግባብነት የሌላቸው ናቸው ሲሉ የገለጹት አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ፣ ህብረተሰቡን የማይወክሉ የጸረ-ሰላም ሃይሎች አቋም የሚንጸባረቅበት ነው በማለት ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን አስታወቅዋል።
መንገስት ህገወጥ ነው ሲሉ የገለጹትን ድርጊት ለመግታት ሃላፊነቱን እንደሚወጣም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለው ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚሚኒስትሩን ጨምሮ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት በማህበራዊ ድረገጾች በኦሮሚያ ክልሎች የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ቅድቀሳ እየተደረገ መሆኑንና መንግስት ለተቃውሞ ሰልፍ እውቅናን እንዳልሰጠ አስታውቀዋል።
ቅዳሜ በመላው ኦሮሚያ ክልል ይካሄዳል የተባለው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በማን አካል የተጠራ መሆኑን አይታወቅም ሲሉ የክልሉ ባለስልጣናት ሃሙስ መግለጻቸው ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment