ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008)
ከሃሙስ ጀምሮ አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ ከተሞች የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተገቢውን አገልግሎት እየሰጠ እንዳልሆነ ታውቋል።
ሃሙስ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ባለስልጣናት በክልሉ የተቃውሞ ሰላምዊ ሰልፍ ለማካሄድ በማህበራዊ ድረገጾች ቅስቀሳ እየተካሄደ ነው ሲሉ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን መግለጻቸው ይታወሳል።
የክልሉ መንግስት ለዚሁ ቅስቀሳ እውቅና እንዳልተሰጠና አዘጋጁ አካል እንደማይታወቅ ቢገለጽም ባለስልጣናቱ የሰጡትን ማሳሰቢያ ተከትሎ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት በተገቢው መልኩ እየሰራ አለመሆኑን ከሃገር ቤት ከተገኘ መረጃ ለመረዳት ተችሏል።
ይሁንና፣ የአገልግሎቱ መስተጓጎል ህገ-ወጥ የተባለውን ቅስቀሳ ለማስቀረት ያለመ ይሁን አይሁን የታወቀ ነገር የለም።
No comments:
Post a Comment