Friday, August 5, 2016

ራያም ወልቃይትም አማራ ነው አማራ ናቸው




እዉነታዉ ይሄ ነዉ በየትኛዉም የኢትዮጵያ ታሪክ ራያ ብሎ ትግሬ፦ወልቃይት ጠገዴ ብሎ ትግሬ የለም፤ራያ የወሎ ክፍለ ሀገር ግዛት ነዉ ወልቃይት ጠገዴ ደግሞ የጎንደር ክፍለ ሀገር ግዛት ነዉ።መተከል አዉራጃ የጎጃም መሬት ነዉ፤ህወሓት በነፍጥ እንጅ መሬት በማመልከቻና በኮሚቴ መቸም አይሰጥም።

የወልቃይት ጠገዴንና የራያን መሬት ለማስመለስ በመጀመሪያ ደረጃ የኢህአዴግ ስርዓት እንክትክቱ መዉጣት አለበት፤ልጅ የአባቱን እርስት ያስከብራል፤የአባቱን እርስት የማያስከብር ልጅ ድቃላ ነዉ፤አንድ ኢንች ሳናስቀር መሬታችንን እናስመልሳለን፤ማንኛዉም የአማራ ልጅ ባለበት ይደራጅ፤ያልመከተ ተፈነከተ፤ያልተደራጀ ተፈጀ።

ማይጨዉ ራሱ የወሎ ግዛት ነዉ፤ማይጨዉን ከወሎ ገንጥሎ ትግሬ ያደረገዉ ዓፄ ዮሐንስ ፬ኛ ነዉ።የራያ ህዝብ ዘሩን የሚቆጥረው ከሰሜን ወሎ ብቻ ሳይሆን እስከ ደቡብ ወሎ ከሚሴ ድረስ ነው።ራያ፣የጁ፣ወረ ባቦ፣ወረ ቃሉ፣ወረ ኢሉ፣ወረ ሂመኖ ከአንድ የዘር ሀረግ የሚመዘዙ ህዝቦች ናቸዉ።


የራያ አዘቦ፣የኦፍላ ወይም ኮረምና የአለማጣ ህዝብ ከወንድሞቹ ከወሎ ህዝብ መለየት የለበትም፤በባህልም ሆነ በቋንቋም የሚመሳሰለው ከራያ ቆቦና ከየጁ ህዝብ ጋር ነው።ቋንቋ መግባቢያ እንጅ ማንነት ሊሆን በጭራሽ አይችልም።

የአላማጣና የራያ አዘቦ ህዝብ አማርኛና የራሱ የሆነ ዘይቤ ያለው ትግርኛ (ድንበርተኛ) ቋንቋ ይናገራል።የኮረም ህዝብ ደግሞ አማርኛ፣አገዉኛና ትግርኛ ይናገራል።

የራያ ቆቦ ህዝብ ሙሉ ለሙሉ አማርኛ ይናገራል።የአላማጣ፣የእንዳ መሆኒ፣የኦፍላና የራያ አዘቦ ወረዳዎች ባህልና ትስስሩ ታሪኩና ግዛትነቱ የወሎ ክፍለ ሀገር እንጅ በታሪክ የትግራይ ሆኖ አያዉቅም፤ራያ ሌላ ትግሬ ሌላ





No comments:

Post a Comment