Friday, June 3, 2016

ሃገርና ሕዝብ የከፋ አደጋ ውስጥ ናቸው::የምንሄድበት መንገድ መፍትሄ አልባ የሚሆነው እስከመቼ ይሆን?


ሃገርና ሕዝብ የከፋ አደጋ ውስጥ ናቸው::የምንሄድበት መንገድ መፍትሄ አልባ የሚሆነው እስከመቼ ይሆን? ‪#
 በቀን በቀን የማንሰማው ጉድ የለም:: ሃገርና ሕዝብ ተሸክመውት የሚገኙት ችግር በሕወሓት መራሽ አገዛዝ የተጫነበቸው መሆኑ ነጋሪ አያሻንም::ሃገርና ሕዝብ ላይ የሚደረጉ በደሎች ከቀን ወደቀን ሲጨምሩ የለውጥ ሃይሉ ከትችት እና ቀልድ አዘር ሂስ ከመፍጠር ውጪ የፈጠረው ብልሃት አሊያም መፍትሄ ስላሌለ አገዛዙ በስህተ ላይ ስህተት እየደረበ እየደራረበ ሃገርና ሕዝብ ለከፋ አደጋ አጋልጧል::እስከመቼ በትችት ብቻ እንደምንኳትን መልስ ሊገኝለት አልተቻለም::እለት ከእለት የምንሰማው የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሃገር ሃብት ዘረፋና ተመሳሳይ ችግሮች በተግባር ስርዓቱ እስካልተመታ ድረስ እንዴት በትችት ብቻ ሊወገድ እንደሚችል አልታወቀም::አገዛዙ የሚሰራቸው ግፎች ከመቀነስ ይልቅ በመጨመር የለውጥ ሃይሉ በአጀንዳ እንዲጠመድ አድርጓል::አንዱን የቀረፈ አስመስሎ አንዱን በመፍጠር አንዱን አስረስቶ በሌላው በማወዛገብ በአድ እሽክርክሪት በማዞር የወሬ ናዳ በመቆለል ትውልዱን እያለታተመው ስልጣኑን በማስረዘም ላይ ይገኛል::
እነ በቀለ ገርባ በባዶ እግራቸው፣ በቁምጣ ፓንት እና በፓካውት ወደ ችሎት ገቡ በማለት ከንፈር በመምጠጥ እና አሳዛኝ ወሬ ከማውራት በጋራ ክንድ አገዛዙን ደቁሰን የሚበደሉ ወገኖቻችንን ነጻ የማናወጣበት ፈጣን ተግባራዊ ስራ የመስራት ግዴታ ከለውጥ ሃይሉ ይጠበቃል::አገዛዙ እጅግ አደገኛ እና ጸረ ሕዝብ መሆኑን ሳናልመው የፈታነው መሆኑ እሙን ሆኖ ሳለ ከማዘን ውጪ ልንፈጥረው የምንችለው ነገር አለመኖሩ ራሳችንን እንድንጠይቅ ግድ ይለናል::በተጨማሪ በባለስልጣናት በተለይ በሕወሓት ሰዎች የሚደረገው ዘረፋ ሌላኛው በትችት ብቻ የምናልፈው ሳይሆን በባለስልጣናቱ ሃብትና ንብረት ላይ ልናደርሰው የሚገባ አደጋ ምንድነው የሚለውንም ማሰብ ያስፈልጋል::አገዛዙ ላይና መሪዎቹ ላይ አስፈላጊ እርምጃዎች ተግባራዊ ስራዎች እስካልተሰሩ ድረስ በትችትና በሹፈት ምን ያህል ዘልቀን እንደምንሄድ ለራሳችንም ሊገባን የማይችል መሆኑ ሲያስደምም በመረጃ መለዋወጥ ብቻ ሳይሆን በተገኙ መረጃዎች ላይ ተግባራዊ ስራ መስራት ካልተቻለ አገዛዙን ከመደገፍ አይለይም::
ኢትዮጵያ ራሳቸው በቻሉ ትናንሽ የቡድን መንግስታት ተከፋፍላ መናበብ በማይችሉ ሕግ አውጪዎች እና ሕግ አስፈጻሚዎች ተቧድና አደጋ ውስጥ ስትሆን ሕዝቡም በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ እየተደቆሰ መገኘቱ አደጋውን የከፋው አድርጎታል::ችግሩ የት ላይ እንዳለ በመለየት አስቸኳይ መፍትሄዎች መተግበር አለባቸው:ልየለውጥ ሃይሉ እርስ በርሱ መመካከር ካልቻለ በማግለል እና በትችት ፖለቲካ በተናጠል መጠመዱ አደጋው እየከፋ እንዲሄድ አድርጎታል:: ወያኤም የለውጥ ሃይሉን እግር እግር እየተከተለ አዳዲስ አጀንዳ በመፍጠር ወጥመድ እያሴረ በስህተት ላይ ስህተትን እየደራረበ በወርጥ ፍሰት ብቻ ፍዘት እንዲፈጠር በማድረግ ለስልጣኑ ምቹ የሆኑ መስመሮችን እየጠረገ ይገኛል::ይህን መገንዘብ ማወቅ መረዳት እና መተግበር ከለውጥ ሃይሉ ይጠበቃል እስከመቼ በትችት ተጠምደን በራሳችን ላይ ጠላት ሆነን ተግባራዊ ስራዎችን በጋራ በመተባበር የማንሰራው ለምን እንደሆነ ግራ ያጋባል::ማንም ሰው በተናጠል የሚያመጣው መፍሄ የለም በሃገራዊ አጀንዳ ትልቅ ተግባራዊ ስራ መስራት ይጠበቅብናል::ሃገርና ሕዝብ የከፋ አደጋ ውስጥ ናቸው::የምንሄድበት መንገድ መፍትሄ አልባ የሚሆነው እስከመቼ ይሆን? ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬
Minilik Salsawi's photo.

No comments:

Post a Comment