Wednesday, June 15, 2016

በራያ ቆቦ ለሆላንድ ድርጅት ነው በሚል ሽፋን ለትግራይ ባለሀብት 160 ሔክታር መሬት ሊሰጥ ነው፡፡



በራያ ቆቦ   ለሆላንድ  ድርጅት ነው በሚል ሽፋን ለትግራይ ባለሀብት 160 ሔክታር መሬት ሊሰጥ ነው፡፡
******************************************************************************
በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ ስር ልዩ ስሙ ጎለሻ የሚባል ቦታ ለሆላንድ ድርጅት ነው በሚል ሽፋን ለትግራይ ባለሀብት 160 ሔክታር በሬት ሊሰጥ ነው ሲሉ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገለፁ ፡፡እንደ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገለፃ ለባለሀብቱ ሊሰጥ የታቀደው መሬት በደን የተሸፈነ ቢሆንም ትእዛዙ ከፌደራል መንግስት በመተላለፉ ደኑን ለመመንጠር እና ለባለሀብቱ ለመስጠት የወረዳው ባለስልጣናት መወሰናቸውን አያይዘው ገልፀዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በህወሀት የንግድ ተቋማት ስር ጥረት በሚል የሚጠራው የዘለቀ እርሻ ማህበር በቆቦ ከተማ ከሚገኘውን አቧሬ ደን 160 ሔክታር በብአዴን እና የህወሀት ከፍተኛ ባለስልጣናት ትዕዛዝ እንዲመነጠር በመደረጉ የድርጅቱም እንቅስቃሴ የደኑን እንጨት በመሸጥ ላይ ብቻ የተወሰነ ሆኖ መቆየቱን በወቅቱ የደኑን መመንጠር ከትሎ የነበረውን የህብረተሰቡን ተቃውሞ ለማቀዝቀዝ ግዙፍ ፋብሪካ አሚናታ የሚባለው ቦታ ላይ ለመገንባት ስምምነት ላይ መደረሱን የከተማው ባለስልጣናት በተለያዩ ስብሰባዎች ሲገልፁ መቆየታቸውንና በመጨረሻ የአዘለቀ እርሻ ተገቢውን ምርት ሊያመርት አልቻለም በሚል ምክንያት መሬቱ ለወልድያ አትክልትና ፍራፍሬ ማህበር ለሚባል አካል መተላለፉን ተከትሎ ህብረተሰቡ በከፍተኛ ሁኔታ ተቃውሞውን እየገለፀ እንደሚገኝ እና አርሶ አደሩ ለረጅም አመታት ጠብቆና ተንከባክቦ ያቆያቸው ደኖች በአምባገነኖች ማናለብኝነት እየተመነጠሩ አካባቢው ለበለጠ በርሀማነት መስፋፋት ተጋላጭ እንዲሆን መደረጉ ስጋት ውስጥ እንደከተታቸው ምነጮቻችን አያይዘው ገልፀዋል፡፡
 Source  – በያሬድ አማረ
Yared Amare's photo.

No comments:

Post a Comment