Friday, June 10, 2016

የመንደር ሌቦችን በመግደል የተጀመረው የወያኔው አገዛዝ የወያኔ ሌቦችን በማውደም ይጠናቀቃል።



የመንደር ሌቦችን በመግደል የተጀመረው የወያኔው አገዛዝ የወያኔ ሌቦችን በማውደም ይጠናቀቃል።
) ኢሕአዴግ ብሎ ራሱን የሚጠራው ሕወሓት መራሹ ቡድን ኣዲስ ኣበባ ሲገባ የኣገዛዙን ወንበር ያስመረቀው በሌቦች ደም ነበር ። እርግጥ የወያኔ ሌብነት የጀመረው ብበረሃ በባንክ ዘረፋ በእርዳታ አህል አና መድሃኒት ዘረፋ ቢሆንም በትጥቅ ትግል መስመር ውስጥ የሚያጋጥሙ ሂደቶች ስለነበሩ ብዙም ትኩረት ኣይሰጣቸውም፥ በሌቦች ደም የተከፈተው የመንግስት ኣስተዳደር ከፍተኛ መንግስታዊ ሌቦችን አና መንግስታዊ ኣሽባሪዎችን ወልዶ አስድጎ ለቱጃርነት አብቅቷቸዋል።
Minilik Salsawi's photo.
የሃይለስላሴ መንግስትና የደርግ መንግስት ውርጃዎች የሆኑ ኣንዳንድ ግለሰቦች የወያኔ ኣገዛዝ በመደገፍ በኣለም ኣቀፍ የዲፕሎማሲ መስክ ሚናዎች ሲጫወቱ ማየት ታላቅ አፍረት ነው። የቀድሞ መንግስት ውርጃዎች ራሳቸው ሌቦች ኣሊያም የሌባ ልጆች ስለሆኑ ከሌባ መንግስት እና ባለስልጣናቱ ጋር ቢተባበሩ ላይደንቀን ይችል ይሆናል ሆኖም በሌቦች ግርግር መሃል የሚዘረፈው የሃገር ሃብትና የሕዝብ ሕይወት ጉዳይ ግን አጅግ ሊያሳስበን ይገባል።ይህ ኣንደኛው ሕዝብን አና ሃገርን ኣደጋ ውስጥ የከተተ ኣደገኛ የማፍያ ተግባር ነው።
የወያኔ ሌቦች ሂሳብ የሚያወራርዱበት ሰዓት ልቃይ ደርሰዋል።ሃገሩን በሰላም ያገለገለ ባለስልጣን የጡረታ ዘመኡን በሰላም አንደሚያሳልፍ ይታወቃል። የወያኔ ባለስልጣናት ግን በስሩት ግፍ እና በፈጸሙት ዘረፋ ከደርግ ባለስልጣናት የባሰ ከባድ ኣደጋ ፊታቸው ላይ ተደቅኖ አየጠበቃቸው መሆኑን ሊያውቁት ይገባል።ህዝብ ከንፈሩን ነክሶ ኣድፍጦ አየጠበቀ ነው።ይህን ደሞ ታውቁታላጩ በኢኮኖሚ ይበላይነት ህዝብን ኣደህይተን አንቆጣጠረዋለን የሚል የሞተ ኣስተሳሰብ በፍጹም ኣይሰራም። ሕዝቡ የኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ስርነቀል ለውጥ ይፈልጋል።የወያኔ ኢኮኖሚ የተገነባው በተጭበረበረ ኢኮኖሚ ላይ መሆኑ ማናችንም የምናውቀው ሃቅ ነው፤የተጭበረበረ ፖለትካ ደግሞ ኣደጋው ከባድ ነው፤ሕዝብ የወያኔ ሌቦችን ሰብስቦ ማቃተሉን በፍጹም ኣይተውም፥፥ኣገዛዙ ከላይ አንስከታች 99% በሌቦች የተሞላ ነው፥ስለዚህ የመንደር ሌቦችን በመግደል የተጀመረው የወያኔው አገዛዝ የወያኔ ሌቦችን በማውደም ይጠናቀቃል። ነጻነት ቀርባለችና ሁላችንም ትግሉን እናጠናክር፤ ይህ የሕዝብ ልጆች ድምጽ ነው

No comments:

Post a Comment