በ25 ዐመት አንድ ደረጃውን የጠበቀ፣ የተሟላ ሆስፒታል መገንባት ያልቻለ “ባለሁለት አሐዝ እድገት” ባፍንጫዮ ይውጣ! (ዘፀአት አናንያ)
እስቲ ተመልከቱ፣ በ25 ዐመታት ውስጥ አንድ የኢህአዴግ ባለስልጣን ታሞ፣ በሐገሩ ታክሞ ድኖ ወይም ሞቶ ያውቃል? 25 ዐመት ሙሉ ለጉንፋኑም፣ለካንሰሩም ባንኮክ፣ ብራስለስ፣ ዱባይ፣ ካሊፎርኒያ ወ.ዘ.ተ ሩጫ ነው፡፡
እስቲ ተመልከቱ፣ በ25 ዐመታት ውስጥ አንድ የኢህአዴግ ባለስልጣን ታሞ፣ በሐገሩ ታክሞ ድኖ ወይም ሞቶ ያውቃል? 25 ዐመት ሙሉ ለጉንፋኑም፣ለካንሰሩም ባንኮክ፣ ብራስለስ፣ ዱባይ፣ ካሊፎርኒያ ወ.ዘ.ተ ሩጫ ነው፡፡
– ጋሽ ግርማ ላለፉት 15 ዐመታት በአማካይ 2 ጊዜ በዐመት ዱባይ ወይም ሳውዲዐረብያ ሔደው ይታከማሉ፤ በእያዳንዱ ጉዞ የሚወጣው ወጪ በሚልዮን የሚቆጠር ነው፤
– አቶ በረከትም የዱባይና ሳውዲ ተመላላሽ ታካሚ ናቸው፤
– አቶ መለስ ብራስለስ ለሕክምና እንደሄዱ ቀሩ፤
– አቶ አለማየሁ ኦቶምሳ ባንኮክ እንደሄዱ ቀሩ፤
– የቤንሻንጉል ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ አሕመድ ናስርም ቢሆኑ ሬሳቸው ከሕንድ ነው የመጣው፤
– አቶ በረከትም የዱባይና ሳውዲ ተመላላሽ ታካሚ ናቸው፤
– አቶ መለስ ብራስለስ ለሕክምና እንደሄዱ ቀሩ፤
– አቶ አለማየሁ ኦቶምሳ ባንኮክ እንደሄዱ ቀሩ፤
– የቤንሻንጉል ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ አሕመድ ናስርም ቢሆኑ ሬሳቸው ከሕንድ ነው የመጣው፤
የኢትዮጵያ ባለስልጣናት እንዴት በ25 ዐመታት አንድ “የሚመጥናቸው” ሆስፒታል እንኳ መገንባት አልቻሉም? እንግዲህ በእውነት በብዙ መመዘኛ (እውቀት፣ ስብእና፣ ራዕይ ወ.ዘ.ተ) እጅግ ያነሱ ሰዎች መሆናቸውን ባውቅም ስልጣኑም፣ ጥይቱም፣ ሐብቱም ይዘዋልና፣ የበላያችን ሆነዋልና…አዎ “የሚመጥናቸው”…እንዴት እንድ “የሚመጥናቸው” ሆስፒታል እንኳ መገንባት አልቻሉም? መች ይሆን እነዚሁ ባለስልጣናት በሐገራቸው የሚታከሙ?
እቺ ሐገር በነዚሁ 25 ዐመታት ባለስልጣናቱን ለማሳከም ስንት የውጪ ምንዛሬ ነው ያወጣችው? ባለፈው አንድ ኮሎኔል ልጁ ታሞበት በውጪ ሐገራት ለማሳከም 3 ሚልዮን ሲያስፈቅድ አይተናል፡፡ ይህ ሰው ልጁ ጉንፋን ቢይዛት 6 ሚልዮን ብር ሊያስፈቅድ ይችላል፡፡
እንግዲህ ከእርሱ በላይ ያሉትን ሰዎች አስቧቸው፡፡ አሁን እንደምናስተውለው በየሐገራቱ ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ዋነኛ ስራ ይህንን የባለስልጣናትንና ዘመዶቻቸውን የሕክምና፣ የማረፍያ፣ የሽርርሽር ቦታዎችን ማመቻቸት ነው፡፡ ይች ሐገር በየዐመቱ የባለስልጣናት ጉንፋን፣ የረገቡ ጡቶች፣ የተሸበሸቡ ፊቶች፣ ብጉር ወ.ዘ.ተ ለማስታመም ለባእዳን ሐገራት ሚልዮኖች አፍሳ የምትሰጥበት ሑኔታ መች ይሆን የሚያበቃው? በዚያ ላይ ባለስልጣናቱን አጅቦ የሚሄድ የአጀብ ጋጋታ አበል አለ፤ ባለስልጣናትና የኤምባሲ ሐላፊዎች ለሕክምና የወጣውን ወጪ በአስርና ሐያ አባዝተው፣ የውሸት ሰነዶች እያዘጋጁ የሕዝብ ሐብት የሚከፋፈሉበት ሑኔታዎች አሉ፡፡ ባለስልጣናቱ በውጪ ሐገሮች በሕክምና እያሉ ሲሞቱም ሬሳ ለማጓጓዝና ሌሎች በርካታ የፕሮቶኮል ስርዐቶች የሚወጣው ወጪ በርካታ ነው፡፡

መች ይሆን የኢትዮጵያ ባለስልጣናት እንደኛው በሐገራቸው የሚታከሙ?
መች ይሆን የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሬሳ ከመንግስት ሆስፒታል የሚወጣው?
እንዴት በ25 ዐመት እንድ “የሚመጥናቸው” ሆስፒታል እንኳ መገንባት አልፈለጉም/አቃታቸው?
መች ይሆን የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሬሳ ከመንግስት ሆስፒታል የሚወጣው?
እንዴት በ25 ዐመት እንድ “የሚመጥናቸው” ሆስፒታል እንኳ መገንባት አልፈለጉም/አቃታቸው?
እነዚህ ሰዎች ወይ እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ጥራታቸውን የጠበቁና “የሚመጥኗቸው” የመንግስት ሆስፒታሎች እንዲያሰሩ፣ አለበለዚያ ደግሞ ለሕክምና ከሔዱበት የባዕድ ሐገር እንዳይመመለሱ የብዙሐኑ ፀሎት ነው፤፡፡
ለሕክምና ከውጭ ሐገር ሔደው እዚያው ሕይወታቸው የምታልፍ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ታሪክ “ሞቱ፣ አረፉ” ሳይሆን “ጠፉ፣ ደመ-ከልብ ሆኑ፣ ተቀሰፉ” ብላ እንድትመዘግበው ያላሳለሰ ጥረት እናደርጋለን፤ በ25 ዐመት የስልጣን ጊዜ አንድ ደሕና ሆስፒታል መገንባት ያልቻለ….ያም ሲያንስበት ነው
No comments:
Post a Comment