Wednesday, June 8, 2016

በባሕር ዳር ለአንድ ቤተሰብ አምስት ዳቦ በፊርማ እየተሸጠ ነው


Muluken Tesfaw's photo.
በባሕር ዳር ዳቦ በፊርማ እየተሸጠ ነው — By Muluken Tesfaw
እንደ ባሕር ዳር ባሉ የዐማራ ክልል ከተሞች ለአንድ ቤተሰብ አምስት ዳቦ በፊርማ ብቻ እንዲገዙ ተደርጓል፡፡ አንድ ቤተሰብ ዐሥር ልጆች ይኑሩት ወይም ከዚያ ያነሰ ዳቦ ቤት ሒዶ ከአምስት ዳቦ በላይ መግዛት አይችልም፤ ለዚያውም በፊርማ፡፡
የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ የዱቄት ፋብሪካዎች የሚያመርቱትን ዱቄት ለዳቦ ጋጋሪዎች አከፋፍላለሁ በሚል ከተቆጣጠረ በኋላ ዱቄቱን ለሕወሓትና ጀሌዎቻቸው በጥቁር ገበያ ያስረክባል፡፡ ለገዢው ቡድን ቅርበት የሌላቸው ባለዳቦ ቤቶች ደግሞ ዱቄት በጣም ትንሽ (ከ10 ኩንታል በወር ያነሰ) ይሰጣቸዋል፡፡
ንግድና ኢንዱስትሪ የሚያከፋፍለው ዱቄት በኩንታል 800.00 ብር ሲሆን በዚሁ ዋጋ የተቀበሉ ጥቅመኞች ደግሞ በጥቁር ገበያ ከ1200.00 እስከ 1400.00 ብር ድረስ ለባለ ዳቦ ቤቶች ያከፋፍላሉ፡፡ በዚህ መሠረት በሕጋዊና በጥቁር ገበያ የሚሸጡ ሁለት የመንግሥት አካላት ተፈጠሩ ማለት ነው፡፡ በጥቁር ገበያ የሚሸጡት የሥርዓቱ ታማኞች አንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ወደ ሚሊኒየርነት ተቀይረዋል፤ ሆኖም ግን አሁንም አልጠገቡም፡፡
ይህ ሁሉ ሆኖ የሚገርመው ግን ከሰሞኑ የዳቦ ቤት ባለንብረቶች ለደንበኞቻቸው ከአምሰት ዳቦ በላይ እንዳይሸጡ መወሰኑ ነው፡፡ የዳቦ ደንበኞችም ዳቦ ቤት ሒደው በመታወቂያቸው ፈርመው ገዝተው መመለስ አለባቸው፡፡
ዐሥር ቤተሰብ ያለው ሰው አንድ ዳቦ ለሁለት ሰው ማካፈል ግድ ሊለው ነው ማለት ነው፡፡ በዳቦ ቤት ሥራ የተሠማሩ ግለሰቦች በዚህ ሳምንት እንደገለጹልኝ ድርጊቱ ለመንግሥት ቅርበት የሌላቸውን ወይም ገልለተኛ አቋም ያላቸውን ነጋዴዎች ከጨዋታ ውጭ ማድረግ ነው፡፡ ለአንድ ሰው አምስት ዳቦ በቀን ተሸጦ ምንም ቢሆን የመብራት፣ የቤት ኪራይና፣ የሠራተኞች ወጭ ችሎ ንግዱ መቀጠል አይችልም፡፡
ይህ የለየለት የዘረፋና የዐማራ ነጋዴዎችን የማደኽየት ሴራ በአስቸኳይ እንዲስተካከል ነጋዴው ብቻም ሳይሆን ተጠቃሚው ሕብረተሰብም ተቃውሞ ማሰማት አለበት፡፡
(መረጃ በመስጠት ለተባበራችሁኝ በባሕር ዳር፣ መራዊና አዲስ ዘመን ከተማ ነዋሪዎች አመሰግናለሁ፤ ወደፊትም ትብብራችሁ እንደሚቀጥል አምናለሁ)

No comments:

Post a Comment