Friday, June 3, 2016

በውጥረት ላይ ያለው የሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ወደ ትምህርታቸው ያልተመለሱ የኢንጂነሪንግ ተማሪዎችን ግቢውን ለቃችሁ ውጡ አለ

(ዘ-ሐበሻ) በውጥረት ላይ ያለው የሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ለአንደኛ ዓመት የኢንጂነሪንግ ተማሪዎች (ስቴንሽን ካምፓስ) ማስጠንቀቂያውን አስተላለፈ:: እንደ ዩኒቨርሲቲው ማስፈራሪያ ከሆነ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ቢጠየቁም እምቢ በማለታቸው እስከነ አካቴው እንደአባረራቸው የሚገልጽ ደብዳቤ በትኗል::
ደብዳቤው እንዲህ ይላል
“ግንቦት 22 ቀን 2008 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባ ያደረገው የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ከግንቦት 23 እስከ ግንቦት 24 2008 ዓ/ም ከቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ክፍል ገበታችሁ ለአንድ ሳምንት ያህል ያቆማችሁትን ትምህርታችሁን መከታተል እንድትቀጥሎ አሳስቢ ለመማር ፈቃደኛ ካልሆናችሁ ግን በገዛ ፈቃዳችሁ ትምህርታችሁን ለመቀጠል የማትፈልጉ መሆናችሁን አውቃችሁ የዩኒቨርሲቲውን ቅጥር ጊቢ ለቃችሁ ወደየቤታችሁ እንድትሄዱ ውሣኔ መወሰኑ ይታወሳል::
“ይሁን እንጂ የዩኒቨርሲቲውን ደንብና የሴኔቱን ውሳኔ ባለማክበር በተሰጣችሁ ሁለት ቀናት የጊዜ ገደብ ውስጥ ትምህርታችሁን መማር እንዳልጀመራችሁ ተረድተናል:: ስለዚህ; የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት ከዛሬ አርብ ግንቦት 26 ቀን 2008 ዓ,ም ጀምሮ መታወቂያችሁን; የምግብ መመገቢያ ካርዳችሁን እና ያለባችሁን ማንኛውንም የዩኒቨርሲቲውን ንብረት እያስረከባችሁ የዩኒቨርሲቲውን ቅጥር ግቢ ለቃችሁ እንድትወጡ እናሳስባለን” ይላል ደብዳቤ::

No comments:

Post a Comment