Saturday, June 4, 2016

በረከት ስምዖን ለህክምና ደቡብ አፍሪካ ሲያመሩ ቢሯቸው ተበረበረ

      (ዘ-ሐበሻ) ሰሞኑን በተቃዋሚዎች በኩል በተለይም አርበኞች ግንቦት 7ን በተመለከተ ‘ጉያችን ስር ነው ያሉት’ የሚል አስተያየት ከሰጡ በኋላ ይህን ማመን በማይፈልጉ የስርዓቱ የጀርባ አንቀሳቃሾች ጥርስ እንደተነከሰባቸው የሚወራላቸው አቶ በረከት ስምዖን ለህክምና ቀጥሮ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዳመሩ ቢሯቸው በደህንነቶች እየተበረበረ መሆኑን የውስጥ ምንጮች አስታወቁ
  በቅርቡ የአቶ በረከትን ቢሮ በተመለከተ አንዳንድ ድረ ገጾች ላይ በተናፈሰ ዜና ምክንያት የበረከት ስሞንን ቢሮ የጎበኙ ግለሰቦች እየታደኑ በመጠናት ላይ ሲሆኑ አንድ የአዲስ አበባ ፌደራል ፖሊስ አባል በዚሁ ምክንያት በቁጥጥር ስር መዋሉንም ምንጮች አስታውቀዋል::
በረከት ስምዖን ለህክምና ቀጠሯቸዉ ወደ ደቡብ አፍሪካ አምርተው እዚያው ይገኛሉ:: በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ቀንደኛ የወያኔ ተቃዋሚዎች እንዳያገኟቸዉ በብሄራዊ መረጃዉ ደህንነት ቅጥረኞች እየተጠበቁ ባሉበት ሁኔታ ከጆሐንስበርግ አጎራባች በሆነችዉ ሳንድተን አካባቢ ከኢንባሲ ጀሌዎች ጋር ታይተዋል በሚል መረጃ የደረሳቸዉ የተቃዋሚ ግብረ ሐይሎች ሳንድተን ከመድረሳቸዉ በፊት አቶ በረከት ቀድመዉ ማምለጣቸዉን መረጃዎች ጠቁመዋል።

No comments:

Post a Comment