ሰሞኑን በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን የስኳር በሽታ መድሐኒት ተገኘ በሚል የተላለፈው መረጃ ስህተት መሆኑን የምግብ፣ የመድሐኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።
ባለስልጣኑ እንደገለጸው፥ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃንና በማሕበራዊ ድረ ገጾች ለስኳር ሕመም መድሐኒት የሚሆን ንጥረ ነገር ከቡና እንደተገኘና በጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና በባለስልጣኑ እውቅና እንደተሰጠው ተደርጎ እየቀረበ ያለው መረጃ የተሳሳተ ነው፡፡
መረጃው ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴርም ሆነ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምንም አይነት እውቅና የሌለው መሆኑንና ጉዳዩ እየተጣራ እንደሆነ ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡
የመድሐኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ዝርዝር ጉዳዩን ለሕዝብ ይፋ የሚደረግ መሆኑን ጠቁሞ፥ ሕብረተሰቡ በተለይም የስኳር ሕሙማን በተሳሳተ መረጃ የተባለውን መድሃኒት እንደይጠቀሙ አሳስቧል።
No comments:
Post a Comment