(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ አተት ተከስቷል:: አሁን ደግሞ ኮሌራ:: በየሰፈሩ ከየቧንቧው የሚፈሰው ውሃ የሚሰቀጥጥ ነው:: በተለምዶ “ይህ ሕዝብ የሚኖርው በኪነጥበቡ ነው” እንደሚሉት አይነት ነው የሰው ኑሮ:: ይህ ከታች የምታዩት ፎቶ በአዲስ አበባ በተለምዶ ጎፋ ማዞሪያ በሚባለው አካባቢ ከሚኖሩ ወገኖች የተገኘ ነው:: ከቧንቧ ውሃውን ሲከፍቱት እንዲህ ያለ ቆሻሻ ውሃ ነው የሚፈሰው:: የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ በሆነችው ከተማ ንጹህ ውሃ ማቅረብ የተሳነው ስርዓት ሕዝቡን በውሃ ወለድ በሽታ እየፈጀው ነው::

No comments:
Post a Comment