Sunday, June 5, 2016

ወታደራዊው ክፍል የኢሕአዴግን ቀውስ አስታኮ ለስልጣን አሰፍስፏል።



ወታደራዊው ክፍል የኢሕአዴግን ቀውስ አስታኮ ለስልጣን አሰፍስፏል።
“ፖለቲካዊ አመራሩ እንጂ ወታደራዊ ክፍሉ ጤነኛ ነው” እሚል መልእክት አደገኛ አካሄድ ነው:: በዝርፊያ በኢኮኖሚ ራሳቸው ያደላደሉ እና የፈረጠሙ ወታደራዊ መኮንኖችን ያቀፈው በሳሞራ የኑስ የሚመራው ወታደሩ ክፍል በሁለት መንገድ የኢሕአዴግን ቀውስ ተከትሎ ስልጣን ሊይዝ ይችላል የሚሉ ፍንጮች አየታዩ ነው። ከዚህ ቀደም የተለቀቁ መረጃዎችን  የሚያጠናክሩ ጽሁፎች መነበብ ጀምረዋል።
ለኢሕአዴግ ቅርብ የሆኑትና የቀድሞ የሕወሓት ታጋይ የነበሩት ጆቤ(ሜጄ አበበ ተክለሃይማኖት) በኢትዮጵያ ደርግነት እያቆጠቆጠ – ዴሞክራሲው እየጨላለመ ነው – ህዝቦች ጠንቀቅ በሉ በማለት ሕዝብን ማስጠንቀቅ ጀምረዋል።ጄኔራሉ በዚህ ጽሁፋቸው ማጣቀሻ በማለት የተጠቀሙት የሳሞራ የኑስን ንግር ሲሆን ወታደራዊው ክፍል በበላይነት ሲቭሉን ስልጣን በቀጥጥሩ ስር ኣድርጎ ሊነዳው አንደሚፈልግ ኣሳይቷል ሲሉ ጽፈዋል፥ ኣያይዘዉም የዴሞክራሲ እጥረት ወይም ምህዳር መጥበብ ማለት ደርግነት መንገስ ማለት ነው፤ ሱፍም ወታደራዊ ልብስም ሊለብስ ይችላል። ብለዋል።
Minilik Salsawi's photo.
በሃገሪቱ የተከሰተውን ግልጽ የፖለቲካ ቀውስ በሃይል የመፍታት ኣዝማሚያ በስፋት አየታየ አየተተገበረ እንደሆነ የሚጠቁመው ጽሁፍ በከፍተኛ አመራሮቹ እየታየ ያለው ነገር አንዳንድ ስጋቶችን እየጫረ ይገኛል።በማለት የመቀሌውን የግንቦት ሃያ ፓናል አንደማጣቀሻ በማስቀመጥ ኢታማዦር ሹሙ ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ያነስዋቸው ሃሳቦችና እና የተናገርዋቸው ነገሮች በጣም እሚያሳዝኑና ሕገ መንግስቱን ገድል ግባ ያሉበት መድረክ ነበር። ከ ሀ እስከ ፐ ስለ ሲቪል አስተዳደሩ ድክመት፣ ልፍስፍስነት፣ ስለ ወታደራዊ ክፍሉ የመተካካት ልዩ ችሎታና ስለ ሰራዊቱ የአሁንና የወደፊት ጥንካሬ ሲያወሩ ላየ ጄኔራሉ ምን እያለ እንደሆነ ይገባዋል ወይ፧ የሚል ጥያቄ ያጭራል። “ፖለቲካዊ አመራሩ እንጂ ወታደራዊ ክፍሉ ጤነኛ ነው” እሚል መልእክት አደገኛ አካሄድ ነው፤ እኔ ልምራ አይነት አንደምታ ያለው ንጝር ነው። የሲቪል መንግስት በወታደራዊ ክፍሉ የሚገመገምበት አሰራርም ሆነ ሕገ መንግስታዊ መርህ ወይም ድንጋጌ የለም። ሲቪል አስተዳደሩ ወታደሩን ሊቆጣጠር ሲገባው በተገላቢጦሽ ወታደራዊ ክፍሉ ሲቪሉን አትረባም፣ ሞተሃል፣ አመራር አታዉቅም እያለው ነው፥ ከኣቶ ኣባይ ጸሃይ በተቃራኒ ሃሳባቸውን የገለጹት ሳሞራ የኑስ ታገልኩለት የሚሉትን ሕገ መንግስት በኣደባባይ ኣፍርሰውታል ብለዋል።
ጄኔራል አበበ(ጆቤ)ደርግነት በሁለት ኢ፡ሕገ መንግስታዊና ስርዓት፡የለሽ በሆነ መንገድ ሊከሰት ይችላል።አንደኛው በግላጭ መፈንቅለ መንግስት ማድረግ ነው። ሁለተኛው የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ብሎም የኢህአዴግ ምክር ቤት ወይም ፈፃሚዉን መመርያ በመስጠትና በማስፈራራት “እከሌ ሊቀ፡መንበር እንዲሆን እከሌን አዉርዱት” ወዘተ በማለት ሊሆን ይችላል። በድርጅቱ ባለው ሁኔታ ይህ አይቻልም ማለት የዋህነት ነው። የግንቦት ሃያ በዓል አስመልክቶ የተደረገው ፓነል ይህን ለማስረገጥ እንዳይሆን መጠንቀቅ አለብን። ኢህአዴግ ዉስጥ ያለው ችግር ባልተመሰቃቀለና ሕገ መንግስታዊ በሆነ መልኩ ከህዝቦች እና ሌሎች ፓርቲዎች ተሁኖ መፈታት ያለበት ጉዳይ ነው፤ ያለ ምንም የወታደር ጣልቃ ገብነት። በማለት በጽሁፋቸው መደምደሚያ ኣስቀምጠዋል፥፥‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬ ሙሉ ጽሁፉን ከዚህ ሊንክ ላይ ያንብቡት።

No comments:

Post a Comment