Thursday, June 23, 2016

ወደድክም ጠላህም ስብሃት ነጋ እና ኢሰያስ አፎርቂ ታላቅ እና ታናሽ (ወንድማሞች ናቸው) ናቸው።

ወደድክም ጠላህም ስብሃት ነጋ እና ኢሰያስ አፎርቂ ታላቅ እና ታናሽ (ወንድማሞች ናቸው) ናቸው። (ናትናኤል ኣስመላሽ)
ከአስመራ ተነስተህ የኢትዮጲያን ህዝብ ነጻ አወጣለሁኝ ብለህ የምታስብ ካለህ አሁንም ሞኝ ነህ። ከደደቢት እና ከሳህል በረሃ ጀምረው አብረው አድገው አስመራ ቤተመንግስት እና አዲስ አበባ ቤተመንግስት ያሉ ሁለት ወንድማማቾች ዛሬም ነገም ፍቅረኛሞች እንጂ ጠላቶች ኣይደሉም። ሞኙ አንተ ግን ኣሁንም ድረስ አስመራ እየ ሄድክ አራት ኪሎ ያለውን ወንድሙን ለመውጋት ታስባለህ። ኣይገባህም እንጂ የስብሃት ነጋ እህት አስመራ ቤተመንግስት ሆኖው ሁሉም ነገር ይታዘባሉ ባንተም ይስቃሉ ከወንድማቸው ስብሃት ነጋ ጋርም ሁሌ ባንተ ይቀልዳሉ። ይህን ሁሉ ነገር እያወቅ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለህ ለውጥ ለማምጣት ታስባለህ።
ለተላላኪነት፣ለእቁብ ሰብሳቢነት አስመራ ዲሲ፣አስመራ ነርወይ ብትመላለስ ከሻእብያ ሳምባ ውጭ መተንፈስ እንደማትችል እወቅ። የሰበሰብከው እቁብ በሻእብያ ካዝና እንጂ ባንተ ካዝና እንደማይቀመጥም ታውቃለህ። አንተም ፖለቲክኛ ሁነህ ህዝቡን ስታጭበረብር ይገርማል። እዛው ለማያቕ በለው፣ ፊሽካው ነፍተህ ነፍተህ የት እንደምትደርስ እናያለን።ለመሆኑ ፊሽካው የት ደረሰ፣ ፊሽካውም ገና ከ ሻእብያ ከንፈር እስክትቀበሉ ድረስ ልንጠብቅ ይሆን?
ህውሓትን መጣል ከፈለክ ኣገር ቤት ለሚታገሉ ወርቅ የሆኑ ኢትዮጲያውያንን በገንዘብ እርዳቸው። አገርቤት ውስጥ ህገመንግስቱን ተከትለው ስለታገሉ ብቻ የሚታሰሩትን ፣ ከስራ የሚባረሩትን ምንም አይነት ገቢ የሌላቸው በገንዘብ እርዳቸው። አንተ የሰበሰብከው እቁብ ለሻእብያ ከምትሰጥ አገር ቤት ላሉ ከልባቸው ለሚታገሉ ወርቅ የሆኑ ኢትዮጲያውያንን ስጥ። እስከ መቼ ነው ለሻእብያ እየገበርክ የምትኖረው።
Natnael Asmelash's photo.
Natnael Asmelash's photo.



No comments:

Post a Comment