Friday, June 17, 2016

በደቡብ ኦሞ ዞን ተማሪዎች ሳይማሩ ለፈተና እንዲቀመጡ ሊደረግ ነው



በደቡብ ኦሞ ዞን ተማሪዎች ሳይማሩ ለፈተና እንዲቀመጡ ሊደረግ ነው//
በተማሪዎችና ቤተሰብ ተቃውሞ ተነስቷል፣ ስለ ቀጣይ ዕድላቸው ሥጋት ተፈጥሯል፡፡
በደቡብ ኦሞ ዞን በደቡብ አሪ ወረዳ በማማ ቀበሌ የሚገኘው የበርካ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ለወራት የሂሳብና ፊዚክስ እንዲሁም አማርኛ ትምህርት ባልተማርንበት ለፈተና እንድንቀመጥ ልንገደድ አይገባም በሚል ባነሱት ተቃውሞ ትምህርት መቋረጡን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል፡፡
የችግሩ መንስኤ የሆነው የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር ከወራት በፊት ሦስት መምህራንን ከት/ቤቱ እንዲነሱና የሶስት ወር ደመወዛቸውን እንዲቀጡ ለወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ጥያቄ በማቅረባቸው መሆኑን መምህራንና ተማሪዎች ያስረዳሉ ፡፡
ምንጮቹ ይህንኑ የተማሪዎች ጥያቄ ተከትሎ በት/ቤቱ ርዕሰ-መምህርና በተማሪዎች መካከል በተነሳው አለመግባባት ፣ ምክትል ርዕሰ-መምህሩና አብዛኛው መምህራን የተማሪዎቹ ጥያቄ አግባብ ነው በማለት ከጎናቸው በመቆማቸው የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር አካባቢውን ለቀው ወደ ዞኑ ዋና ከተማ-ጂንካ ከሄዱ ሁለት ሳምንት ያለፋቸው በመሆኑ፣ ለወራት አማርኛ፣ ፊዚክስና ሂሳብ ያለመማራቸውና የዓመቱ መጨረሻ ፈተና ጉዳይ ተማሪዎችንና ቤተሰባቸውን በእጅጉ እንዳሳሰባቸው አሳውቀዋል ፡፡
ይህን ክስተት በሚመለከት የትምህርት ባለሙያዎች ሁኔታውን ‹በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ

No comments:

Post a Comment