የወያኔ የፕሮፓጋንዳ ማሽን የሆነው ራዲዮ ፋና ተቋርጦ የነበረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሃምሌ 4 ቀን እስከ ሃምሌ 7 2008 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ በመግለጽ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፈተናው ጊዜ ከረመዳን ጾም ጋር የተገናኘ መሆኑን በመግለጽ ለተማሪዎች ከጾሙ በኋላ ፈተናው እንዲሰጥ መጠየቁን ተከትሎ ሊወሰን እንደቻለ የሽፈራው ሽጉጤን ቢሮ ጠቅሶ ኣንብቦልናል፥ ሆኖም ውሸት የማይሰለቸው ወያኔ ሕዝቡ በኣክቲቭስቶች እየተመራ በፈጠረበት ጫና በሕዝብ መገደዱን በመካዱ ራሱ ተለጣፊ ኣድርጎ ባቆማቸው አሕበሾች መልካም ፈቃድ የተገኘ ኣድርጎ ለመስበክ ሞክሯል።
የፈተናው ቀን ለሁለት ወር አንዲራዘም የኦሮሞ ኣክቲቪስቶች የጠየቁ ቢሆን የሕዝቡ ጥያቀ ኣሁንም እንዳልተመለሰ እየተናገሩ ይገኛሉ፤የኦሮሞ ተማሪዎች ላ6 ወራት ያህል ከፖሊስ ጋር በመፋጠጥ ለመብታቸው ሲታገሩ ትምሕርት ኣቋርጠው የነበረ ቢሆንም የወያኔ ኣገዛ በበቂ ሁኔታ ያልተማሩ ተማሪዎች ፈተና እንዲቀመጡ በማስገደዱ ፈተናው ተሰርቆ ሊቋረጥ መቻሉ ሲታወቅ በቀጣይነትም ጥያቄው መልስ እስካላገኘ ድረስ የተቃውሞ አንቅስቃሴ እንደሚደረግ ታውቋል።
ከታች የሚታየው ምስል የ፩፪ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሙስሊም በአል ላይ መደረጉን እንቃወማለን መንግስት ጊዜውን በአስቸኩይ ይቀይርልን ። በማለት ሕዝቡ ኣደባባይ ወጥቶ ከተቃወመበት ሰልፎች ኣንዱ ነው።
No comments:
Post a Comment