Saturday, June 11, 2016

በዘረፋ የሚታወቁት ኦሕዴዶች ወይንስ ሕወሓቶች ? በኢትዮጵያ የተንሰራፋውን ሙስና ለማቆም መጀመሪያ አናቱን መምታት ያስፈልጋል። ከፍተኛ የሆነ የተመላሽ በጀት ዘረፋ ተካሂዷል።


በሙስና ስም በቅርቡ እየተለቀሙ የሚገኙት (የሚለቀሙ) የኦሕዴድ ባለስልጣናት በቅርቡ ከኦሮሚያ ኣከብቢ የተነሳው የሕዝብ አመጽ ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ብተፈጠረ የፖለቲካ ኣለመግባባት ሰለባ የሆኑ አንደሆነ ጊዜው ራሱ ምስክር ነው፥አቶ በረከት ስምዖን ከኣቦይ ስብሃት ጋር በተነታረኩበት የኢሕአዴግ ስብሰባ ላይ የሕወሓት ከፍተኛ ኣመራሮች እና አባላትን የሃብት ክምችት በተመለከተ በጥናታዊ ሪፖርት ባሉት ላይ ዘርዘር ኣድርገው በማቅረብ ከኣቦይ ስብሃት ሞት ጠሪ የሚል የብስጭት መልስ እስኪሰጣቸው ድረስ በሃገሪቱ ላይ ከባድ ኣደጋ ጋርጦ የሚገኘው የባለስልጣናት ዘረፋ በሕዝቡ ዘንድ በስፋት እንደሚታወቅ አስቀምጠታል፤ ኣቶ በረከትም ቢሆኑ ለዘረፋ የዋዛ ኣይደሉም ከሃገር ውስጥ ትልልቅ ሆቴሎች ባለንብረትነት ጀምሮ አስከ ኢምሬት አና ማሌዢያ ሪያል አስቴቶች ባለንብረት ናቸው።
ኢሕአዴግ ውስጥ ሕወሓቶች በበላይነት ከፍተኛውን ዘረፋ በመፈጸም ሲታወቁ የብ አዴን አና ኦህዴድ ኣመራሮችን ደሞ ከዘረፋው እንዲሊሱ የሚያደርጉት ራሳቸው የሕወሓት ኣመራሮች ናቸው፤በስራቸው በምክትልነት የሚሾሙት የሕወሓት ኣባላት ከተልእኳቸው ኣንዱ ባለስልጣናትን እያሳሳቱ ሙሰኛ በማድረግ የፖለቲካ ኣለመግባባት በተፈጠረ ሰኣት ሁሉ ለማፈን አንዲሁም ባለስልጣናቱን በማሰር የሕዝብን ቀልብ ለማሞኘት የሚጠቀሙበት ስልት ነው፥ አስካሁን በሙስና ታስረው የተፈቱ ይሁኑ የታሰሩት የፖለቲካ ጉዳዮች ሰለባ የሆኑ የወያኔ ባለስልጣናት ናቸው፥ከበላይ ያለው አናቱ እንኳ ሊነካ በተባባሰ መልኩ ዘረፋውን ተያይዞታል።ከ2007 በተመደበ የሃገሪቱ በጀት ላይ ያልተሰራበት አና ተመላሽ ሊሆን የሚገባው ገንዘብ መስሪያ ቤቶች በተለያየ ሰበብ ለመመለስ ፈቃደኛ እንዳልሆኑና እስካሁን የዘገዩበትንም ምክንያት ለመግለጽ አንደማይፈልጉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ያስረዳሉ። የ2008 ላይም ተመላኅ ሊሆን ይችላል ተብሎ የተገመተ ያልተሰራበት በጀት አስካሁን በተጠናው መሰረት 46% ሲሆን ጥናቱ ሲጠናቀቅ ከዚህም በላይ አንደሚሆን አና ያለፈው ኣመት ችግር አንደሚደገም ስጋት ኣለ።
ሕዝብን ኣፈናቅሎ ሜዳ ላይ ኣፍስሶ ለባለስልጣናትና ወዳጆቻቸው የጎልፍ መጫወቻና መዝናኛ ስፍራ የሚገነባ ጨቋኝ ኣገዛዝ በየትኛውም መንገድ ቢሆን መቀጠል የለበትም፥በሙስና ስም በቅርቡ እየተለቀሙ የሚገኙት የሚለቀሙ)የኦሕዴድ ባለስልጣናት በቅርቡ ከኦሮሚያ ኣከብቢ የተነሳው የሕዝብ አመጽ ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ ብተፈጠረ የፖለቲካ ኣለመግባባት ሰለባ የሆኑ አንደሆነ ጊዜው ራሱ ምስክር ነው፤በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ግድያዎችን እና ኣፈናዎችን በመቃወማቸው ብቻ በሙስና ስም እስር ቤት አንዲገቡ መደረጉ አጅግ ኣስገራሚ ሲሆን በኢትዮጵያ የተንሰራፋውን ሙስና ለማቆም መጀመሪያ አናቱን መምታት ያስፈልጋል

No comments:

Post a Comment