ትዝብት … የእስራኤል መንግስት ማንኛውንም አደጋ ላይ ያለ ዜጋውን በሰላም የማስመለስ ሃላፊነት አለበት!!! የአይምሮ ችግር ያለበት ይህ ኢትዮ – እስራኤላዊ በጋዛ ሰርጥ በሃማስ ቁጥጥር ስር ከዋለ እንሆ 658 ቀናቶችን እያስቆጠረ ነው።
ከሁሉም ከሁሉም እጅጉን የሚያሳፍረው የእስራኤል መንግስት ለቤተሰቦቹ ወደ “ሚዲያ እንዳትወጡ እኛ ውስጥ ውስጡን እየሰራን ነው” ቢሉም እስካሁን ምንም አይነት አዲስ ነገር የለም ከቀናቶች መሮጥና ከአበራ በጋዛ ሰርጥ በሃማስ እጅ መሰቃየት ባሻገር። ሆኖም በስተመጨረሻ የወላጅ ነገር የልጃቸውን ናፍቆት አልቻሉምና ስሜታቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው እናት አባት ወንድም …ወ.ዘ.ተ ለ እስራኤል ሚዲያ ሽፋን እንዲሰጣቸው ጭሆታቸውን ቢያሰሙም ሚዲያውም ዝም መንግስቱም ዝም ሆኗል ነገሩ።
አስታውሳለሁ ጊላድ ሻሊት በጋዛ ሰርጥ በሃማስ እጅ በነበረበት ጊዜ .. ከጥዋት እስከማታ ሳንወድ በግዳችን ማለት ይቻላል ስለዚህ ወታደር ብቻ ነበር የምንሰማው በየቴሌቪዥን መስኮቶች በየ ድረ ገጾች .. እንዲሁም በየጎድናው አስፓልት ዳር የሚሰቀሉትን ፖስተሮች ይህ ነው ልላቹህ ይከብዳል። አበራ መንግስቱን ለማስመለስ ምን እየተሰራ ነው? ሚዲያውስ ለምን የሚጠበቅበትን ሽፋን አይሰትም ? አበራ መንግስቱን ለማስለቀቅ የተቋቋመ የግብረ ሰናይ ድርጅት አለ ወይ ? ካለስ ምን ምን ሰርቷል? የ ቤተ እስራኤሉ ማህበርስ ምን እየሰራ ነው ከወላጆች ጎን በመቆም ምን ድጋፍ ሰጠ ? ይህን ኢትዮ እስራኤላዊ ወጣት በሰላም ወደ ወላጆቹ ለመጨመር የሁላችንም ድጋፍ ያስፈልል። ሌላው እንደ አስተያየት አድርጌ የማቀርበው ለሚዲያዎች ባጠቃላይ ያለ እረፍት በየቀኑ ቀኑ በሶሻል ሚዲያዎች አማካኝነት በውስጥ መስመር ስለዚህ ወጣት ማስታወስ ይኖርብናል።መልካም ቀን !
No comments:
Post a Comment