Sunday, June 26, 2016

በተናጠል እየሄድንበት ያለው መንገድ አስጊም አደገኛም ሲልም ሊወጡት የማይችሉ አዘቅት ነው


በተናጠል እየሄድንበት ያለው መንገድ አስጊም አደገኛም ሲልም ሊወጡት የማይችሉ አዘቅት ነው::
 አንድ ነን እያልን ራሳችንን አየሸነገልን አናታለው፤እጅለእጅ ተያይዘን ወያኔን የመጣል ታሪካዊ የትውልድ ግዴታ ኣለብን። ኢትዮጵያዊነት ችሮታ አሊያም ስጦታ ሲልም በደረጃ የሚሰጥ ዜግነት ሳይሆን የእያንዳንዱ ሕዝብ የማንነት መሰረት የተፈጥሮ ማሕተብ እና የውርስ አደራ የታላቅነት ተምሳሌት ነው – ኢትዮጵያዊነት!!! በዚህ ሀገር ፖለቲካ ውስጥ የኢትዮጵያዊነት የደረጃ መዳቢ አድርጎ እራሱን ያስቀመጠው አደገኛ የአመለካከት ቡድን እስከአሁን በመወራጨት ላይ እንዳለ ነው።በአንድነት ሽፋን ዳግም ቅኝ ግዛት የለም::የህዝብን ትግል ለማስጠበቅ የሕዝብን ነጻነት ለማረጋገጥ ሕዝቦችን ያማከለ የጋራ አንድነታችንን ማጠናከር ግድ የሚልበት እና ሃገራዊ/ህዝባዊ ሃላፊነታችንን በመወጣት ወሳኝ ወቅት ላይ መሆናችንን አውቀን የትግል ቃልኪዳናችንን በማጥበቅ ህዝባዊ ድሎችን ማረጋገጥ ሃገራዊ ግዴታችን እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባል::
እውነትን እና ስልጡን ፖለቲካን ቢተናነቀንም እንደምንም ልንውጠው ግድ ይላል::ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል ነው::እየሄድንበት ያለው መንገድ አስጊም አደገኛም ሲልም ሊወጡት የማይችሉ አዘቅት ነው::በፈረንጅ አገር ወያኔ በግልጽም ይሁን በተዘዋዋሪ የላካቸው ባለስኮላርሺፖች አዛኝ ቂቤ አንጓች የአንድነት ሃይል መስለው ሰርገው በመግባት እየሰሩ ያለው ስራ እጅግ ያሳዝናል::ከመወራጨት ውጪ ከነአጨብጫቢዎቻቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ እንደማያመጡና የለውጥ እንቅፋት እንደሆኑ ልንነግራቸው ይገባል::የሚዲያ ተቋማት እና የድህረገጽ ውጤቶች ሕዝብን በማስተማር ሕዝብን መብቱን እና ነጻነቱን አውቆ ለሌላው እንዲያስተምር በማድረግ ረገድ አስፈላጊውን ወቅታዊ መረጃ እና መነሳሳትን በማስረጽ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል።
ያለፉ እና የከሰሙ ወሬዎችን እና አሉባልታዎችን ከመርጨት የወያኔ የፈጠራ አደናባሪ እና አዘናጊ አጀንዳዎችን እኝኝ በማለት ከማውራት ብሄር ተኮር ክፋፋይ ሃሳቦችን ከማርከፍከፍ አዛኝ መሳይ መርዝ ሃሳቦችን ከመናገር ተቆጥበን ሕዝቡን ስለመብቱ እና ነጻነቱን በማስተማር ረገድ መትጋት ከተያዘ ለውጥ የማይመጣበት ምንም ምክንያት የለም። ትችትን እና ሂስን ላለመዋጥ እውነትን ላለመቀበል የሚደረጉ ሩጫዎች ታጥቦ ጭቃ እንጂ የትም እንደማያደርሱ እንዲሁም ፓርቲዎችን እና ሰዎችን መፈረጅ እና መወንጀል ሃሳቦችን ማጣጣል ምንም ለውጥ እንደማያመጣ ካለፈው ተምረናል ። ያሳልፍነው የትግል ሂደት ከጭብጨባ እና ስብሰባ ያለፈ ፋይዳ እንዳሌለው ተገንዝበን የወሬ እና ሆይሆይ ትግል ስለማያዋጣ ጥንካሬን እና ለውጥን የምናመጣበትን የትግል ስልት በመመካከር እና በመወያየት ሃሳብን በማቻቻል መረጃ በመለዋወጥ ሃገራዊ የጋራ አጀንዳ ሊኖረን ይገባል እላለሁ።ልዩነትን በማቻቻል በጋራ መታገል ችላ የማይባል ሃገራዊ አጀንዳ ነው

No comments:

Post a Comment