Saturday, June 11, 2016

መንግስታዊ ሽብር ከሚጠበቀው በላይ ኣድጓል። የአምባገነኖች መጨረሻ ውርደት እና ሞት ነው።


መንግስታዊ ሽብር ከሚጠበቀው በላይ ኣድጓል። የአምባገነኖች መጨረሻ ውርደት እና ሞት ነው።
የደሕንነት ተቋሙ ያደራጃቸው የዘራፊ ቡድኖች ከንጹሃን የንግድ ሰዎች ላይ ዘረፋ አያካሄዱ መሆኑ፣ በኮንሶና ኣከባቢው እንዲሁም በዳባት ሕዝባዊ እምቢተኝነት መቀጣጠሉ፣ በኦሮሚያ አና ኣማራ ክልል ተቃውሞ ይፈናዳል ተብሎ መሰጋቱ ፣ዜጎች ከቤት ንብረታቸው በማናለብኝነት አየፈናቀሉ ሜዳ ላይ መጣላቸው፣የፖለቲካ ጫናውና የኢኮኖሚ ዘረፋው መጧጧፉ ፣የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ገፈፋና በሞኖፖል መያዝ ወዘተ ያልው ስርዓት በራሱ ኣለመተማመኑንና አየዘመመ ለመውደቅ ማጋደሉን ያመለክታል። ሕዝቦች ሃሳባቸውን በነጻነት እንዳይገልጹ አሳሪ ሕጎችን በመተግበር የዜጎችን መብት እና የሕግ የበላይነትን ቀብረውት በትንንሽ የመንደር ካድሬዎች ሃገርና ሕዝብ በስቃይና መከራ ቋፍ ውስጥ ይገኛሉ።
የወያኔ ኣምባገነን ኣገዛዝ የፈጠረው ስርዓት አልበኝነት አገራችንን ወደ ከፋ መቀመቅ እየከተተ ነው።ሕወሓት መራሹ ኣገዛዝ የሚመራቸው የደህንነትና መከላከያ ሃይሎች በሕዝብ ላይ የሚያደርሱት ኣፈና እና ግድያ እንደቀጠለ ነው።በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች የተሰማሩ መንግስታዊ አሸባሪዎች ከእለት እለት የሚፈጥሩት ችግሮች በመጨመሩ ሃገሪቷ መንግስት ኣልባ መሆኗን በገሃድ እያረጋገጠ ነው።
የሕዝብን ኣንድነት ንዶ የተበጣጠሰች ኢትዮጵያን በመፍጠር በጎሳ እርስ በርስ ለማባላት ለሕዝብ ጦርነት አየደገሰ የሚገኘው የወያኔ ጉጅሌ ኣገዛዝ ራሳቸውን በኢኮኖሚ ያፈረጠሙ ባለስልታናትን አና ጋሻ ጃግሬዎቻቸውን በበላይነት ደሃውን ሕዝብ እየረገጡ እስከመቼ አንደሚቀጥሉ ኣጠያያቂ ነው፥ሃገራችን እና ሕዝባችን ነጻነታቸውን እና መብታቸውን ለማስከበር ቆራጥ እና ጽኑ የትግል ኣመራር የሚፈጽም ቆራጥ ልጆችን ይፈልጋሉ። ኣምባገነኖች ላለፉት ረዥም ኣመታት በሕዝብ ጫንቃ ላይ ተቀምተው ሲጨቁኑ በተላያየ ኣጋጣሚዎች በሕዝብ ኣመጽ ከስልጣናቸው ተገፍትረው ተጥለዋል፥ በመልካም ኣስተዳደር እና በፍትሕ ማጣት እየተሰቃየ የሚገኘው ሕዝብ ጠንካራ እና ስር ነቀል ለውጥ ይፈልጋል።ይህን ለማግኘት ደሞ ሁላችንም በመረባረብ የዜግነት ግዴታችንን ልንወጣ ይገባል።የጋራ ጠላት የሆነውን መንግስታዊ ኣሸባሪ ስርዓት ለማስወገድ ሁሉም ሃላፊነት ኣለበት።ለተተኪው ትውልድ ከጭቆና የጸዳች ኢትዮጵያን ለማስረከብ መረባረብ ያለብን ወሳኝ ወቅት ላይ ነን። የአምባገነኖች መጨረሻ ውርደት እና ሞት ነው። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬
Minilik Salsawi's photo.

No comments:

Post a Comment