Thursday, June 23, 2016

አይሲስ ኢትዮጵያንን መግደሉን ለመቃውም ሰልፍ በመውጣቷ 6 ወር የተፈረደባት ሜሮን አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቀለች


semayawi party
(ዘ-ሐበሻ) አይሲስ በሊቢያ ኢትዮጵያውያንን መግደሉን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት በጉዳዩ ላይ ያሳየውን ቸልተኝነት በመቃወም በተጠራው ሰልፍ ላይ በመውጣት ‹ወያኔ ሌባ፣ መንግስት የለም፣ አትነሳም ወይ፣ የታረደው ወገን ያነተ አይደለም ወይ›› በሚል ሁከትና ብጥብጥ ፈጥራለች በሚል ተከሳ 6 ወር ተፈርዶባት የነበረችው የሰማያዊ ፓርቲ አባሏ ሜሮን አለማየሁ አርበኞች ግንባርን በኤርትራ መቀላቀሏን አስታወቀች::
በአርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ ላይ ቀርባ ከአስመራ የሰማያዊ ፓርቲ አባልና የአዲስ አበባ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባል ሀገር ቤትበነበረችበት ወቅት በሕወሓት መንግስት የደረሰባትን መከራ ያስረዳችው ሜሮን ኢትዮጵያን ነፃ ለማውጣት ያለው አማራጭ ቆርጦ ጫካ መግባትና ጠመንጃ መያዝ ነው ብላለች::

No comments:

Post a Comment