Thursday, June 30, 2016

ሃብታሙ አያሌው ለሕክምና የውጪ ጉዞ መከልከል ኣገዛዙን ዋጋ ያስከፍለዋል።


ሃብታሙ አያሌው ለሕክምና የውጪ ጉዞ መከልከል ኣገዛዙን ዋጋ ያስከፍለዋል።ሰብዓዊነት በፖለቲካ አንድነት ወይም ልዩነት አይለካም።
J የነጻነት ታጋይ እና የቁም እስረኛ የሆነው አቶ ሃብታሙ ኣያሌውን በተመለከተ ከሆስፒታል የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ሕመሙ ከመባሱ ውጪ የተሻሻለ ነገር ኣለመኖሩን ሲጠቁሙ ለማስታገሻ የተባለውም መድሃኒት እስካሁን ፍንጭ ኣለማሳየቱ ታውቋል፥ኣቶ ሃብታሙ ከኣለቃ ጸጋዬ በርሄ በወረደ ትእዛዝ ፍርድ ቤት ከሃገር እንዳይወጣ ስላገደው በቂ ሕክምና ማግኘት ኣልቻለም፥ከሃገር ወጥቶ በቂ ሕክምና እንዲያገኝ በኣዲስ ኣበባ የሚገኙ ዲፕሎማቶችን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ጫና በማድረግ ላይ ሲሆኑ ለፍርድ ቤት የቀለበ ኣቤቱታ መልስ ውጤቱ ባይታወቅም የሕወሓት ባለስልጣናት በስብሰባ እና በስራ እያሳበቡ ጉዳዩን እየጎተቱን ይገኛሉ።
Minilik Salsawi's photo.
አቶ ሃብታሙ አያሌው ለሕመም የተዳረገው በሕወሓት የማሰቃያ ማእከል በሆነው የማእከላዊ ጨለማ በደረሰበት ከፍተኛ ድብደባ እና ስቃይ ለሕመሙ መንስኤ እንደሆነ ይታወቃል፥ ሃብታሙ በኣንድ ወቅት ሲናገር ፦ በማእከላዊ ምርመራ በምደረግበት ወቅት ልብሴ በደም ርሶ መቆም እያቃተኝ ተንበርከኬም ቢሆን የሚፈልገውን እንዲጠይቀኝ መርማሪውን ብማጸነውም እየሳቀ ረጅሙን ዘመን ትቀመጣለህ ይለኝ ነበር ።ከሰው ተገልዬ ብቻ ሳይሆን ከሚጠጣም ውሃ እንኩዋን እንዳልገናኝ ከፍተኛ ክልከላ ይደረግብኝ ነበር። ብሏል።በተጨማሪም ወደ እስር ቤት ከተዘዋወረ በኋላ በተለያየ ጊዜ ሕክምና እንዲፈቀድለት ጠይቆ ፍርድ ቤት ይሁን ወሕኒ ቤት ልመፍቀድ ባለመፈለጋቸው ኣሁን ላለበት ከባድ ሕመም ተዳርጓል፤ ለዚህ ደሞ ተጠያቂው የሕወሓት ኣገዛዝ መሆኑ ኣይካድም፥ ኣገዛዙ ወንጀለኛ ነው፥እንደ ሃብታሙ ባሉ ንጹሃን ላይ የሚሰራው ግፍ ወንጀለኛ መሆኑ በቂ ምስክር ነው።
ሃብታሙ ኣያሌው የፖለቲካ እምነቱን በነጻነት ስላራመደ ነጻነቱ ተገፉ በእስር ማቋል፥ይህ ደግሞ ለሕዝብ ልጆች ነጻነት ሲል የተከፈለ መስዕዋትነት ስለሆነ የሕዝብ ልጆች በሃብታሙ ኣያሌው ላይ በወያኔ ኣገዛዝ የሚፈጸመውን ግፍ ኣጥብቀን እንቃወማለን እናወግዛለን ለፍት ሕ መታገላችንንም እንቀጥላለን፥ የወያኔ ኣገዛዝ ኣፋጣኝ በሆነ ሁነታ ኣሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የሃብታሙን ጤንነት በቂ ሕክምና እንዲያገኝ የውጪ ጉዞ እገዳው የማንሳት ግዴታ ኣለበት።በዝጥጎች ላይ የሚደረግ ሽብር ሊቆም ይገባል።‪ሰብዓዊነት በፖለቲካ አንድነት ወይም ልዩነት አይለካም። #‎ምንሊክሳልሳዊ‬

No comments:

Post a Comment