በሳምረ ሰሓርቲ ወረዳ ባምባ ቀበሌ በድርቅ የተጠቃ ህዝብ የኣስቸኳይ እርዳታ ሊከፋፈል ተብሎ የመጣው እህል “የማደበርያ ዕዳቹ የማትከፍሉ ከሆነ ኣትሰጡም” በማለት እርዳታው ሳይሰጡ ወደ የቤቱ ከመለሱት በኋላ ቅዳሜ 23/ 09/08 ዓ/ም በሶስት ኣይሱዙ መኪኖች ጭነው ወደ መቐለ ሲያጓጉዙት ጣሺ በሚባል ቀበሌ ሌሊት በህዝቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የእርዳታ እህል የመዳበርያ እህል ካልከፈላቹ ኣንሰጥም ብሎ መዝረፍ በትግራይ መላ ወረዳዎች የሚከወን የዘወትር የካድሬዎች ስራ ነው።
በኣሁኑ ወቅት ድርቅ ባስከተለው ረሃብ ህዝቡ ለፍተኛ ጉዳት ተዳርጎ ይገኛል።
የረሃቡ ጉዳት ትኩረት ሊስብ ባለመቻሉ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው።
የረሃቡ ጉዳት ትኩረት ሊስብ ባለመቻሉ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው።
የዘንድሮ ድርቅ በርካታ የሰው ሂወት መቅሰፉና እየቀሰፈም እንዳለ ይታወቃል።
No comments:
Post a Comment