Thursday, June 9, 2016

የኢንተርኔት ኣጠቃቀም ሕግ (ወጥመድ) የተባለው ተቃዋሚዎችን ለማፈን እንጂ ሃገርና ሕዝብን ለመጥቀም አልጸደቀም።


የኢንተርኔት ኣጠቃቀም ሕግ (ወጥመድ) የተባለው ተቃዋሚዎችን ለማፈን እንጂ ሃገርና ሕዝብን ለመጥቀም አልጸደቀም።
Minilik Salsawi's photo.
  የዳባት ሕዝብ የቀድሞ ወታደራዊ መንግስት ለህዝብ አገልግሎት እንዲውል ተክሎት የነበረውን ዘመናዊ ትራንስፎርመር ወደ ትግራይ ሊያጓጉዙ የነበሩ የሕወሓት ሌቦች ተሳቢ መኪኖች በህዝቡ ተቃጥለው ሹፌሮቹም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሰምተናል፥ይህን የመሰለ የተደራጀ መንግስታዊ ሌብነት ሕግ እያስፈለገው በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የሳይበር ኣክቲቭስቶችን ኣፍኖ እስር ቤት ለማጎር የኢንተርኔት ኣጠቃቀምን ይተመለከተ ሕግ ስለ ኢንተርኔት ጥቅም በማያውቁ ተከራክረው መናገር በማይችሉ እጅ ኣውጪዎች ሕግ መውጣቱ ያለው ኣገዛዝ ለስልጣን ያለውን ገብጋብነት ሌላኛው ማረጋገጫ ነው።
ወያኔ በስልጣኑ ላይ ይደርሳሉ የሚላቸውን የሳይበር ጥቃቶች ለመከላከል በኮምፒዩተር ወንጀል ኣዋጅ ስም ዜጎችን በማፈን ወደ ጨላማ ቤት ለመወረር አንዲያመቸው የዘየደው ዘዴ አንጂ በውስጡ ለታቀፋቸው ገዳዮች አና ዘራፊዎች ሊጠቀመው ያወታው ኣዋጅ ኣይደለም፤ ከሽብርተኝነት ኣዋጁ የታዘብነው ያየነው የተለማመድነው ነገር ቢኖር የተቃዋሚ ኣመራሮችን ጋዝጠኞችን አና መሰል ዜጎችን በማፈን በማሰር ረዥም ኣመታት በመፍረድ ሕግን ለሕገወጥነት ሲውል ነው።የጸረ ሽብር ሕጉ እንደ ኣልቃይዳ አና ኣልሽባብ ያሉ ኣለም ኣቀፍ ኣሽባሪዎችን ለማደን በሚል በኣለም ኣቀፍ ደረጃ የጸደቀ ቢሆንም የወያኔው ኣገዛ ግን ሕዝቦችን ለማሳቀቅ ለማፈን ለማሰር ተጠቅሞበታል አየተጠቀመበት ይገኛል፥ ይህም የኮምፒዩተር ወንጀል መከላከል ሕግ የተባለውም ከዚህ የተለየ ኣላማና ግብ የለውም።
ያለፈቃድ ኮምፒውተሮችን መሰርሰርና መሰለል ቅጣት ያስከትላል የሚለው ሕግ ለኣገዛዙ ተቅWማት ግን አንደፈለጉ አንዲሰልሉና አንዲሰረስሩ ከዚህ ቀደም በስውር የሚያደርጉትን ሕገወጥነት በኣይን ፍጥጥ አንዲያደርጉ ኣውጆላቸዋል።የኣገዛዙ የደህንነት ተቋም የኮምፒውተር ስርሰራ (ሃችኪንግ)፣ የይለፍ ቃልና ሌሎች የደህንነት አጥሮችን ሰብሮ መግባት (ብረኣኪንግ ጸቹሪትይ መኣሱረስ)፣ ክፍያ የሚጠይቁ የኮምፒውተር አገልግሎቶችን ያለክፍያ መጠቀም፣ ከባለቤቱ ወይንም ሥልጣን ካለው አካል ፈቃድ ውጪ በኮምኒዩኬሽን ሂደት ላይ ያለን የኮምፒውተር ዳታ ወይም የዳታ ፕሮሰሲንግ አገልግሎት መከታተል፣ መቅዳት፣ ማዳመጥ፣ መውሰድ፣ ማየት፣ መቆጣጠር ወይም ሌላ ተመሳሳይ ሕገወጥ ተግባር ሲሰራ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን ኣሁን ደግሞ በኮምፒዩተር ሕግ ሽፋን ለተኃለ ህገወጥነት ራሱን ኣደላድሎ ኣዘጋጅቷል።
በዜጎች ላይ ከፍተኛ መንግስታዊ ሽብር የሚፈጽመው የወያኔ ኣገዛዝ በስልጣን የመቆየት ፍላጎቱን ለማሳካት በከፍተኛ ገንዘብ አጅግ ኣደገኘ የሆኑ የሳይበር ጥቃቶች በሃገር ውስጥ አና በውጪ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አና ተቋማት ላይ ሲፈጽም አንደነበር የቅርብ ጊዜ መረጃዎችን ኣንብበናል።ይህን ወንጀሉን በሕግ ለማስደገፍ አንዲረዳው ያወጣው ኣዋጅ አንጂ ሕዝብና ኣገርን ለመጥቀ የጸደቀ ኣዋጅ ወያኔ የለውም ኣይኖረውም።የኢንተርኔት ኣጠቃቀም ሕግ የተባለው ተቃዋሚዎችን ለማፈን እንጂ ሃገርና ሕዝብን ለመጥቀም አልጸደቀም። ይህን ወንጀለኛ ኣገዛዝ ልናፈርሰው ግድ ይላል

No comments:

Post a Comment