Thursday, June 23, 2016

ጀነራል ከማል ገልቹ በሻእብያ ሳንባ ስለማይተነፍሱ ለ15 አመታት ቁም እስረኛ ሆነዋል።

ጀነራል ከማል ገልቹ በሻእብያ ሳንባ ስለማይተነፍሱ ለ15 አመታት ቁም እስረኛ ሆነዋል።
ይህ ሰው ጀነራል ከማል ገልቹ ይባላል፣ ጀግና ብቻ ሳይሆን አገር ወዳድም ነው። ለኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው የኢትዮጲያ ህዝብ ነጻነት የሚታገል ጀግና ነበር። በሂወቱ ለሚያምንበት ነገር የማይደራደር ጀግና ነው። ይህ የኢትዮጲያዊነት ስሜቱ ደግሞ የበለጠ መስዋእትነት እንዲከፍል አድርጎታል። አስመራ የገባው ብቻውን ሳይሆን ለውጥ ፈላጊ ወታደሮቹን አስከትሎ ነው።
አሁን ከማል ገልቹ የት ገባ? ከማል ገልቹ ለመብቱ ለመታገል ከማንም የሻእብያ ባለስልጣን ተጽኖ ነጻ ሆኖ መታገልን ስለመረጠ ብቻ አስመራ ቪላጆ በተባለ ቦታ ውስጥ ቁም እስረኛ ሆኖ ይገኛል። ከዚህም አልፎ የኤርትራው ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፎርቂ ከኢትዮጲያ መከላከያ ሰራዊት 55 % የኦሮሞ ተወላጆች ስለሆኑ፣ ከማል ገልቹን በብዛት መቀላቀል ስለጀመሩ የኦሮሞን ወደስልጣን መምጣት ያሰጋቸው የኤርትራው ፕረዚዳንት ከማል ገልቹን ከፖለቲካ ጨዋታ ውጭ ኣድርጎዋቸዋል።
ጀነራል ከማል ገልቹ በሻእብያ ሳንባ ስለማይተነፍሱ ለ15 አመታት ቁም እስረኛ ሆነዋል። እነ እንትና ግን አስመራ ሳይገቡ አሜሪካ እያሉ ሳንባቸው ለሻእብያ ስላስረከቡ አስመራ አሜሪካ ወይንም አስመራ አውሮፓን ናዝሬት አዲስ አበባን አድርገው እንደፈለጉ በፈለጉበት ጊዜ ይገባሉ ይወጣሉ። የነ እንትና ዋና ስራ የኤርትራው ፕረዚዳንት እና ቤተሰቦቻቸውን የአናናር ዘዴ ለኢትዮጲያ ህዝብ መንገር ወይንም ማስተላለፍ ነው። ወደድክም ጠላህም በሻእብያ ሳንባ እያተነፈስክ ኢትዮጲያ ውስጥ ለውጥ አመጣለሁኝ ብለህ እንዳታስብ!!! እንትና ከከማል ገልቹ በላይ አስመራ አሜሪካን አዲስ አበባ ላንጋኖ ያደረግከው በሻእብያ ሳምባ ስለምትተነፍስ ነው። ከማል ገልጁ ግን በሻእብያ ሳምባ ኣልተነፍስም ስላለ አስመራ ውስጥ ለ ተከታታይ 15 አመታት የቁም እስረኛ ሆኖ ይገኛል።
ልብ በል የ ኦሮሞ ህዝብ ብዛቱ ከማንም ቢሄር በላይ ነው፣ አሜሪካ እና አውሮፓ ያሉ የኦሮሞ ተወላጆች ለከማል ገልቹ የትኬት ዶላር ያጡ እንዳይመስልህ!!! ይህ የኦሮሞ ጀግና ግን እንዳንተው ተላላኪ፣እቁብ ሰብሳቢ፣ባንዳ ስላልሆነ ነው እስካሁን ድረስ መግባት እና መውጣት ያልቻለው። ስለዚህ አንተ በሻእብያ ሳምባ እስከተነፈስክ ድረስ፣ ፊሽካውን ሻእብያ እስከነፋው ድረስ ካለህበት አንድም እርምጃ ንቅንቅ እንደማትል እወቅ!!! ከድሃው ዳያስፖራ እየሰበሰብክ ለሻእብያ የምት ሰጠው ዶላር አገር ቤት ላሉ የፖለቲካ እስረኞች ብት ሰጥ ይሻላል። አገር ቤት ውስጥ ህገ መንግስቱን አክብረው ስለታገሉ ብቻ ከስራ ተባረው ምንም ገቢ የሌላቸው እንደ ከማል ገልቹ ወርቅ የሆኑ ኢትዮጲያውያን አሉ እና እነሱን እርዳቸው። ከዚህ በተረፈ ግን በሻእብያ ትንፋሽ የተነፋው ፊሽካ እንካንስ የኢትዮጲያ ድምበር ሊያልፍ የአስመራን ድምበርም ኣያልፍም!!!
Natnael Asmelash's photo.



1

No comments:

Post a Comment