Sunday, June 12, 2016

ቴዲ አፍሮ 40ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ከወደቁትን አንሱ አረጋውያን ጋር ሊያከብር ነው

(ዘ-ሐበሻ) አንድናቂዎቹ “የኢትዮጵያ ሙዚቃ አብዮተኛ; የፍቅር ንጉሥ; የፍቅር መልዕከተኛ ወዘተ…” እያሉ የሚጠሩት ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ 40ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ከተቸገሩ አረጋውያን ጋር አብሮ ሊያከብር መሆኑ ተሰማ:: ለዘ-ሐበሻ የደረሱት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ቴዲ አፍሮ እነዚህ አረጋውያንን የሚረዱበት ማዕከልን ይረዳል::
ቴዲ አፍሮ 40ኛ ዓመቱን የሚደፍነው ሐምሌ 7, 2008 ዓ.ም ሲሆን በዓሉን የሚያከብረውን የወደቁትን አንሱ የአረጋውያን ማዕከል ውስጥ እንደሆነና ይህ ተቋም ከሚረዳቸው አረጋውያን ጋር እንደሆነ ታውቋል::
ይህን የልደት በዓል በማስመልከትም ለነዚህ አረጋውያን የተዘጋጀ ነገር እንዳለም ተሰምቷል::
ቴዲ አፍሮ 37ኛ ዓመቱን ያከበረው የዘ-ሐበሻ አዘጋጆች በሚኒሶታ ባዘጋጁት የሙዚቃ ኮንሰርት ቀን መድረክ ላይ እንደነበር ይታወሳል::
ቴዲ አፍሮ በሰብአዊ ጉዳዮች ላይ ሲሳተፍ ይህ የመጀመሪያው አይደለም:: ከዚህ ቀደም ካደረጋቸው በርካታ በጎ ተግባሮች መካከል የሰው ሕይወት አጥፍቷል በሚል በአሥር ቀናት ውስጥ በሞት እንዲቀጣ ወይም የነፍስ ዋጋ 700 ሺሕ ብር እንዲከፍል የፍርድ ውሳኔ ተላልፎበት፣ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ሙሉ ክፍያውን (700 ሺሕ ብር) ከፍሎ ያተረፈው ኢትዮጵያዊው አስመሮም ኃይለ ሥላሴ ገብረ ኢየሱስ ይጠቀሳል::
በተጨማሪም ቴዲ አፍሮ ታስሮ ከተፈታ በኋላ ወላጆቻቸ
ውን ላጡ ህፃናት መርጃ የሚውል የሙዚቃ ኮንሰርት በአዲስ አበባ ስታዲየም አዘጋጅቶ ሙሉ ገቢውን ሰጥቷል:: በተጨማሪም ለአበበች ጎበና ህፃናት ማሳደጊያም በተለያዩ ጊዜያት ድጋፍ ሲያደርግ ነበር::
በሌላ በኩል ቴዲ አፍሮ አዲሱን የሙዚቃ አልበሙን እንደጨረሰና ይህም ሥራው ለኢትዮጵያ አዲስ አመት ይለቀቃል ተብሎ ይጠበቃል::

No comments:

Post a Comment