Monday, June 27, 2016

ጵጵስናና ፈተናው


ጵጵስና በምድር የከበረ በሰማይ የተመረጠ ሹመት ነው ። ለአማኞች ሞገስ ሊኢአማንያን ደግሞ ፈተና ነው፡፡ የማያምኑባቸው ሰዎች ከብረው ሲያቸው ኢአማንያን ይበሳጫሉ፡፡ ደግሞም የእነሱ ባለመሆናቸው አቃለው ወይም አናንቀው እንዲያም ሲል ሰድበው ለሰዳቢ በመስጠት ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ይጥራሉ። የአማኞች ልቡናን እሰከመከፋፈል ይደርሳሉ። ይህ በዘመን ብዛት የታየ እውነት ነው፡፡ አሁን ግን ግራ የሚያጋባው አማኞች እራሳቸው በግሩፕና በመንደር ተከፋፍለው የሚያደርጉት የስም ማጥፋት ዘመቻ ወሰን አልፎ የመጨረሻውን እስልጣን አካል የሆነውን ሲኖዶሱን ህልውና ላይ ሁኗል ሲኖዶስ ማለት ቀኖና የሚያወጣ የሚያስተካክል የቤተክርስቲያን እራስ መሆኑን ቀስበቀስ እንዲረሳ፤ ቀኖና የመደገግ አቅሙም እንዲያንስ ቢያወጣም ተቀባይነት እንዳይኖረው የሚደርግ ዘመቻ ወደመሆን ተለውጧል። ይህ ለአማኞች ወድቀት፤ ለሃይማኖቱም ዋጋ የሚያስከፍል የመጀመሪያው መጨረሻ ነው።
ለሲኖዶስ ክብር የማይሰጥ ህዝብ ለጳጳስ አይታዘዝም ለጳጳስ የማይታዘዝ ለቤተክርስቲያን ሥራዓት አይገዛም ይህ ደግሞ ለካህኑም የክህነት አገልግሎት ዋጋ መስጠት ይቀርና ካህኑም ቅጥረኛ ምዕመኑን የቤተክርስቲያን ተመላላሽ ብቻ ይሆናል ። ይህ ማለት ያለ ዋጋ በሃሳብ የሚደክሙ የእግዚአበእሔር በረከት የተለያቸው አማኞች በዙ ማለት ነው ።ይህን ማንም አይፈልገውም ሲሰማም የሚቀፍ ነው ግን እየተደረገ ያለ ሃቅ ነው። ዛሬ አባቶችን የሚያከብር ፤ከሊቃውንቱ ስር ሁኖ የሚጠይቅ ብርቅ የሆነበት ዘመን ላይ ደርሰናል። የጵጵስናን መንፈሳዊ ሃይልነትም ወደመርሳት አዘንብለናል። ጵጵስናን የምመዝነውም በተሾሆሙት አባቶች ልክ ብቻ እየሆነም ነው። በመሰረቱ ጵጵስና ሌላ ተሾአሚም ሌላ ነው፡፡ሁልጊዜም ሁሉ እንደፈለጉት አይገጥም ሁሉም ደግሞ ልክ አይሆንም ሁሉም ልክ ቢሆን ኑሮ መምረጥ ለምን አስፈለለገን መርጠን የገዛነው ሁሉ እንደፈለግነው ሁኖም አያውቅም፡፡ ማበላለጥና ፣ማድነቅን የመሳሰሉት እኮ የሚመጡት ተመሳሳይ በሆነ ቦታ ተመሳሳይ ሰዎች ተገኝተው በሚሰጡት አገልግሎትና ወሳኔ፤ ንግግርና ምክር ተበላልጠው ስለሚገኙ ነው ። በተሿሚዎች አባቶች በኩልም ይህ ሊኖር ግድ ነው ግን አናዳቸውን በምንፈልግበት ሌላኛውን አናገኝ ይሆናል ያንዳቸውን ክፍተት አንዳቸው ይሞላሉ ብሎ ማሰቡ ተገቢ ነው ሁልጊዜ ሰው ፍጹም አይደለምና ከአንድ ብርቱ ሁለት መዳሃኔቱ የሚለውም ቃል ከዚህ ላይ ይሰራል በዘመኑ ካለው ህዝብ መካከል የተመረጡ ስለሆነ ችግር እንኳን ቢኖርባቸው የትውልዱ ነጸብራቅ ናቸው እናም አባቶች እናክብር።
በርግጥ ጵጵስና ፈተና የሆነበት ዘመን ላይ ነው ያለነው ግብጾችን ስናመልክ ኑረን የእኛ የምንላቸው ሲሾሙ ከመጀመሪያው ጀምሮ በሽኩቻና በመንድር ተቧድነን ስማቸው ስናጠፋ ችሎታቸውን ስንደብቅ ኑረናል ፡እየኖርንም ነው ።ጣሊያን የገደላቸውን አቡነ ጴጥሮስና አቡነ ሚካኤል በመቃብር እንኳን ስናበላልጥ! ከሞት ባሻገር ላለው አለም አንዱን ቅዱስ ሌላውን ግን አስታዋሽ የለሽ አድርገናል ። የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እንደ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ቲዎፍሎስ ያለ መሪና በቀደመ ስማቸው ሊቀ ሥልጣናት የአሁኑ ብጹእ አቡነ መልከ ጼዴቅ የመሰለ ታታሪና ትጉህ ሠራተኛ አታገኝም ።ለነዚህ አባቶች የተሰጠው ክብር ስናየው እጅግ ያሳዝናል የስራ ችሎታ የሌላቸው ሰዎች ስራቸው ሲያደናቅፉ፤ ስማቸው ሲያጠፉ፤ በማያውቃቸው ትውልድ እንዲሰደቡ ክፉ መርዝ ዘርተው ያለፉ ብቻ ሳይሆን ያሉም አሉ። እኛም እያየን ፣እየሰማን ኑረናል እየኖርንም ነው። ግን እስከመቼ? ጵጵስና ክብሩ አንሶ ፈተናው በዝቷል። የሚሾሙ አባቶች እውቀታቸው ሳይሆን የተውልድ ሥፍራቸው እየተመዘነ ሃጢያታቸው በዝቶ በአማኙ ዘንድ እንዲጠሉ ማድረግ ቋሚ ሥራ ሁኗል። ለክርስትናውና ለቤተክርስቲያኒቱ ግን ሸክም እየሆነ ነው። ክርስትና ከመንደር ከወጣ ሁለት ሽህ ዓመት አልፎታል ከገሊላ መንደር የተመረጡት አሥራ ሁለቱ ሃዋሪያት ዓለምን ዙረው ክርስትናን የዓለም ሃይማኖት ካደርጉት ቆይተዋል ።
ጠባብ አስተሳሰብ የያዙ ሰዎች በመንደር እድንወስነው ወስነው ስለመንደር ይነግሩናል። እኛ ጳጳስ የሚያስፍልግ መሆኑን ስናምን እነሱ የየት መንደር ሰው ጳጳስ መሆን እንዳለበት ይጨነቃሉ። የሚፈለገው ጳጳስ ወይስ አጎት። ስንላቸው የብሄር ብሄረ ሰብእ ጉዳይ ያነሳሉ ክርስትና በብሄር አልተቋቋም የተመሰረተው ከአንድ መንደር ቢሆንም የዓለም ሁኗል ሲባሉ አይገባቸውም እንዲገባቸውም አይፈልጉም ይልቁንም ብዙ ችሎታ ያላቸውን አባቶች፤ በጥቂት ለሥራ ያልተጠሩ ለወሬ የተፈጠሩ በሚመስሉ ሰዎች ሞራላቸው እየተነካ፤ ስራቸው እየተዳከመ፤ የተፈለገው የአንድነትና የፍቅር አገልግሎት፤ የአባትነትና የልጅነት መንፈስ እየራቀ፤ ልዩነቱም ከጊዜ ወደጊዜ እየሰፋ እንዲመጣ አድርገዋል ። የዚህ ክፉ ሥራ ተጠያቂው ወሬ ናፋቂው ትውልድ ነው ዓለም ቴክኖሌጅ ፈጥሮ ለመታወቅና ለመሸለም ሲሮጥ የእኛዎቹ ወሬ ፈጥረው እሮጣሉ፡፡ ታሪክ አዛብተው ይጽፋሉ፡ የእነሱ ሃሳብ ደጋፊ ወይም መንደርተኛ ካልሆነ በስድብ ናዳ ያዎርዱበታል ዓለም ሁሉ እንዲጠላው አቅማቸው በፈቀደ መጠን ይጥራሉ። ግን ለምን ? ዓላማቸውና ግባቸው ምንድነው? በርግጥ ይህን ጥያቄ ቢጠየቁ መልሳቸው ምንእንደሆነ አይታወቅም ከሁኔታዎቹ ግን ተነስቶ መተንተን ይቻላል ።
ይቀጥላል
ሊቀ መራህያን ነኝ
ማንኛውም ሰው እውነቱን ማወቅ ከፈለገ በንጹህ አይምሮ
በዚህ እሜል ሊያገኘኝ ይችላል jemis1968@gmail.com

No comments:

Post a Comment