መንግስታችን አስጊ ናቸው የተሰጣቸውን ስራ ከመስራት ይልቅ የመንግስታችን ምስጢሮች ለማወቅ ያነፈንፋሉ ብሎ የፈረጃቸውን ከኣዲስ ኣበባ ፖሊስ ለሲቪል ደህንነት የወሰዳቸውን 347 ኣባላቱን ወደ ቀድሞው የፖሊስ ስራቸው መመለሱ ውስጥ ኣዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል፥ምንጮቹ ምናልባት ከፖሊስነት ስራቸው በተደራቢነት የስለላ ስራ ሊሰሩ አንደሚችሉ ይህ ለመንግስት ኣስጊ ናቸው የተባለው ፍረጃ ሽፋን ሊሆን ይችላል ሲሉ ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል።ኣባላቱ ከተበተኑበት ተሰብስበው ወደየቀድሞ ክፍላቸው እንዲሄዱ እና ሪፖርት እንዲያደርጉ የተነገራቸው ባለፈው ሃሙስ ሲሆን አስካሁን 179 ሰዎች ስራ ሲጀምሩ ቀሪዎቹ በየክፍላቸው ካለስራ ውለው ወደየቤታቸው እየተመለሱ እንደሚገኙ ምንጮቹ ገልጸዋል።
ከኣዲስ ኣበባ ፖሊስ ወደ ደህንነት ቢሮ የተወሰዱት ፖሊሶች ጦላይ በሚገኘው ምስጢራዊ የደህንነት ማሰልጣኛ የሶስት ወር ትምህርት የተከታተሉ ሲሆን በዚሁ ማሰልጣኛ ማእከል ውስጥ ከተለያዩ ሃገራት የተሰበሰቡ የትግራይ ተወላጅና ኤርትራውያን ዲያስፖራዎች በስልጣና ላይ እንደሚገኙ ምንጮቹ አክለው ተናግረዋል፥ወደ ቀድሞ የፖሊስነት ስራቸው የተመለሱ ኣባላት ውስጥ የሕወሓት ሰዎች እንደሌሉበት የገለጹት ምንጮቹ ፖሊሶቹ ወደ ስራቸው ሲመለሱ ተሰናብተው ነው ይባል እንጂ ምናልባት ከፖሊስነት ስራቸው በተደራቢነት የስለላ ስራ ሊሰሩ አንደሚችሉ ይህ ለመንግስት ኣስጊ ናቸው የተባለው ፍረጃ ሽፋን ሊሆን ይችላል ሲሉ ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል
No comments:
Post a Comment