Tuesday, June 14, 2016

የደሕንነት ቢሮው ስብሰባና የመኮንኖች ጉርምርምታ … ዝም ያለ ሁሉ ሞኝ ኣይደለም:: ‪


የጦርነት ወሬ ሕዝቡን ኣንገሽግሾታል።ለእናት ኣገር መሞትን የሚጠላ ማንም የለም።በደርግ ስርዓት በኣንድነት ሽፋን ከፈቃደኛ ዘማቾች ጀምሮ እስከ ታፍሰው የዘመቱ ከብሄራዊ ውትድርና ጀምሮ አስከ ለብለብ ሰልጣኝ ተማሪዎች ወታደራዊ ኣምባገነኖችን በስልጣን ለማቆየት በተደረገ ጦርነት ሲሰዉ የደርግ መኮንኖች ለ ኤምፔሪያሊስት ሃይሎች አና ቅጥረኞቻቸው ወያኔና ሻእቢያ ኣገሪቷን ኣሳልፈው ሸጠው ወታደሩን ሜዳ ላይ ለማኝ ኣድርገውታል፤ቀጣዩም የወያኔ ኣምባገነን የወንበዴዎች ቡድን በባድመ ምክንያት ባደረገው ጦርነት ከ፹ ሺህ በላይ የሚልቁ ዜጎች ደመ ከልብ በማድረግ ኣላማውን ዘንግቶ ውነቱን በመካድ ወጣቱን ደመ ከልብ ኣድርጎታል፤በዚህ ደግሞ ሕዝቡ ትልቅ ቂም ቋጥሯል ስለዚህ ይህን ሕዝብ ጦርነት ኣለብኝ ና ዝመት ከሚባል መሃል ኣገር የተሰቀለውን ኣገዛዝ ቢያወርድ ይቀለዋል።
ሕዝቡ ካለፉት ኣገዛዞች ይሁን ኣሁን ካለው ዘረኛ ኣገዛዝ ብዙ ተምሯል፥ዝም ያለ ሁሉ ሞኝ ኣይደለም፤ ጊዜና ወቅት ይጠብቃል።መሃል ኣገር ላይ ተዘፍዝፎ ሃገርና ሕዝብን አያሰቃየ ለሚኖር ኣገዛዝ መዝመት ሳይሆን መሳሪያውን ወደ ኣገዛዙ ማዞር ጽድቅ ነው፥የወያኔ ኣገዛዝ በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ ኤርትራ ላይ ያወጣውን ዘገባ ተከትሎ ሲያራግብ የነበረ ሲሆን ጉዳዩን ኣመድ በዱቄት ይስቃል ኣድርጎታል፥የሚሉሽን ባልሰማሽ እንደተባለው የራሱን ጉድ ምን እንደሚባል እያወቀ እና እየሰማ ባልሰማ ሙድ የራሱን እያሳረረ የሌላውን ሲያማስል ሰሚ ጆሮ ሊያገኝ ባለመቻሉ ኣትኩሮት በማስፈለጉ የድንበር ላይ ጦርነት ገጥሟል፥ችግሮቻችንን የምንፈታው መሃል አገር ላይ የተሰቀለውን ኣገዛዝ በማውረድ እንጂ ከጎረቤቶች በመዋጋት ኣይደለም።ጦርነትን ኣስመልክቶ ከኣምባገነኖች ጎን መቆም የሕዝብን ስቃይ በማበርታት የጨቋኞችን እድሜ ማስረዘም ነው።

No comments:

Post a Comment