Monday, June 13, 2016

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ የተነሳ ድንገተኛ የእሳት አደጋ በሰዉ ህይወት ምንም ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉን ዩኒቨርስቲዉ አስታወቀ፡፡

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ የተነሳ ድንገተኛ የእሳት አደጋ በሰዉ ህይወት ምንም ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉን ዩኒቨርስቲዉ አስታወቀ፡፡
የእሳት አደጋዉ የደረሰዉ ዛሬ ከሰዓት በኋላ 9፡00 ሰዓት አካባቢ ነዉ፡፡ የዪኒቨርስቲዉ አስተዳደርና የተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ቢሆነኝ አያሌዉ እንደገለፁት የእሳት አደጋዉ የደረሰዉ ባለ ሁለት ፎቅ በሆነ አንድ ህንፃ ላይ ነዉ፡፡ በዚህም ሁለተኛ ፎቅ ላይ የሚገኙት 18 የተማሪዎች ማደሪያ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል ፡፡ በሰዉ ህይወት ላይ ግን ምንም አይነት አደጋ አልደረሰም ብለዋል፡፡
ምክትል ፕሬዝዳንቱ እንደተናገሩት የአደጋዉ ምክንያት አልታወቀም፤ጉዳዩም እየተጣራ ይገኛል፡፡ ተማሪዎች በማደሪያቸዉ ዉስጥ የኤሌክትሪክ ምድጃ መጠቀማቸዉ ለአደጋዉ ዋንኛ ምክንያት ሊሆን እንደሚችልም ተገምቷል፡፡
በቀጣይም የእሳት አደጋን ለመከላከል በሁሉም ህንፃዎች የእሳት አደጋ መከላከያዎች ተገጥመዉ አገልግሎት እንዲሰጡና የኤሌክትሪክ መስመሮችም በባለሙያ እንዲፈተሹ ይደረጋል ብለዋል፡፡
የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር የወልድያ ከተማ አስተዳደር ዉሃና ፍሳሽ አግልግሎት፣ፖሊስና የአካባቢዉ ባለሃብቶች ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል፡፡

Amhara Mass Media Agency's photo.

No comments:

Post a Comment