Wednesday, June 8, 2016

የዲሲ ግብረሃይል ለአርቲስቶች ማስጠንቀቂያ ሰጠ | መግለጫውን ይዘናል

(ዘ-ሐበሻ) በሼህ መሀመድ አላሙዲ “የደም ገንዘብ” ይደገፋል የሚባለውንና በሰሜን አሜሪካ ያለውን የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽንና ህዝቡን ለመከፋፈል ተቋቁሟል የሚባለውን ኤኢሳ ዋን (AESA ONE) ለሚተባበሩ አርቲስቶች የዲሲ ግብርሃይል ማስጠንቀቂያ ሰጠ:: ከዚህ ቀደም እነ ሐመልማል አባተ; ሽዋፈራው ደሳለኝ; ደረጀ ደገፋው; ን የመሳሰሉ የስርዓቱ ተላላኪ አርቲስቶች ላይ የማያዳግም ቅጣት የጣለው የዲሲው ግብረሃይል “ኢትዮጵያዊ ክብርና ሞገሳችንን ገፈው ህዝባችንን መቀለጃ የሚያደርጉ አርቲስቶችን ቦይኮት እናደርጋለን” ሲል መግለጫ አውጥቷል::
የደም ገንዘብ አጓጉቷቸው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚቀልዱትን አርቲስቶች ማንነት ተራ በተራ በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ እናቀርባለን::
መግለጫው እንደሚከተለው ተስተናግዷል:-
ከዲሲ ግብረ ሀይል የተሰጠ መግለጫ! ሼር በማድረግ እንተባበር!
በኤኢሳ ዋን (AESA ONE) ላይ መሳተፍ በወገናችን እልቂት መቀለድ ነው !!
ኢትዮጵያዊ ክብርና ሞገሳችንን ገፈው ህዝባችንን ጥሪቱን አሟጠው በንቀት እየተጫወቱ ያሉት ቡድኖች የሀገር ውስጡ አልበቃ ብሏቸው እነሆ ላለፋት 4 ዓመታት በውጭ ያለውን ኢትዮጵያዊ ለመበታተን ያደረጉትን ሴራ ህዝባችን አንድ በመሆን በቂ ምላሽ ሰጥቶ አክሽፎታል፤ ሆኖም ዛሬም ለ33 አመታት የቆየውን የሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌዴሬሽናችንን ከኢትዮጵያ ህዝብ በግፍ በተዘረፈ የደም ገንዘብ ሊበታትኑት ኢትዮጵያን በኢንቨስትመንት ስም እራቁቷን እያስቀራት ባለው አላሙዲ አማካኝነት ለአምስተኛ ግዜ ቨርጂኒያ አሌክሳንድሪያ ውስጥ በሚገኘው ማውንት ቨርነን ሃይ ስኩል ከጁላይ 3 እስከ ጁላይ 9 የሚካሄድ የመከፋፈያ ዝግጅታቸውን አዘጋጅተዋል።
በዚህ ኢትዮጵያውያንን ለመከፋፈል በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ ማንኛውም አገር ወዳድ ባለመካፈል ወገናዊነታችሁን እንድታሳዩ ጥሪአችንን እያስተላለፍን፤ በተጨማሪም አርቲስቶቻችንን ክብር የሰጣችሁ ወገናችሁን ፀረ ኢትዮጵያ በሆነ ዝግጅት ላይ ባለመካፈል አጋርነታችሁን አሳዩ እያልን፤ በዚህ የደም ዝግጅት ላይ የወገናችሁን እልቂት ችላ ብላችሁ በምትሳተፉ አርቲስቶች ላይ ማህበረሰቡ በማናቸውም ዝግጅቶቻችሁ ላይ ማእቀብ (boycott) እንደሚያደርግባችሁ ከወዲሁ ልትረዱት ይገባል ።
ይህንኑ ዝግጅትም በመቃወም በዲሲ እና አካባቢው የሚገኙ ሀገር ወዳዶች የተለያዩ የተቃውሞ ዝግጅቶች ያዘጋጁ መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን።
የዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል!!!

No comments:

Post a Comment