Thursday, June 16, 2016

በጾረና ግንባር በተደረገ ጦርነት ከ200 በላይ ገድዬ ከ300 በላይ የሕወሓት ወታደሮችን አቁስያለሁ ሲል የሻእቢያ መንግስት ኣስታወቀ።‪



በጾረና ግንባር በተደረገ ጦርነት ከ200 በላይ ገድዬ ከ300 በላይ የሕወሓት ወታደሮችን አቁስያለሁ ሲል የሻእቢያ መንግስት ኣስታወቀ።
የሻእቢያ የማስታወቂያ ሚኒስቴር በዛሬው እለት በለቀቀው መግለጫ ከወያኔ ሰራዊት ጋር በጾረና ግንባር ከእሁድ እስከ ሰኞ ጠዋት ባደረገው ውጊያ ከ200 በላይ የወያኔ ወታደሮችን ገድሎ ከ300 በላይ ማቆሰሉን በመግለጫው ኣትቷል።መግለጫው እጅግ በርካታ መስዋትነት የተከፈለበት ያለው ይህ ጦርነት የወያኔ ወታደሮች ከነበሩበት ቦታ በማፈግፈግ መሸሻቸውን ጠቅሷል።
ይህ ደም ኣፋሳሽ ጦርነት ለምን ተካሄደ በምንስ ምክንያት ለምንስ ኣላማ ሲል የጠየቀው መግለጫው ራሳቸው ወረውን ራሳቸው ጉዳተኛ ሆነው እፍረትን ተከናንበዋል ብሏል፤ ለመሸፋፈን ቢሞክሩም ተጋልጠዋል ሲል ሚኒስቴሩ ጽፏል።ከፍተኛ የፖለቲካና ዲፕሎማቲክ ኪሳራ ተከናንበዋል ሲል ማስታወቂያ ሚኒስቴሩ ኣስቀምጧል።
Minilik Salsawi's photo.

No comments:

Post a Comment