ሙስና በኦሮምያ DW Amharic
በዚህ ባሳለፍነዉ ሁለት ወራት ዉስጥ የኦሮሚያ ክልል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚገኙ የአመራርና የሥራ ኃላፊዎችን በቁጥጥር ሥር እያዋለ መሆኑ እየተነገረ ነዉ።
የቀድሞ የኦሮምያ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ዘላም ጀማህን ጨምሮ፣ የሱሉልታ ምክትል ካንትባ የነበሩት አቶ ዲሮ ዳሜ፣ የላገ ዳዲ ለጋ ጣፎ ከንቲባ የነበሩት አቶ ፋሲል ኃይሉ፤ የቀድሞ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዓለሙ ለሜሳ፣ የቀድሞ የጋላን ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ ሙሉጌታ ከበደ እንዲሁም ሌሎች 10 ግለሰቦች አንድ ወር ባለሞላ ጊዜ ዉስጥ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ አገር ዉስጥ ያሉ ዘገባዎች ያመለክታሉ።
የኦሮሚያ ክልል ሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ክሱን ስመሰርት እኝ ግለሰቦች ስልጣናቸዉን በመጠቀም ኃብት አከብተዋል፤ አብዛኞቹም ተከሰሾችም መሬት እና መሬት ነክ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ሙስና ፈጽመዋል ሲል ወንጅሏቸዋል። የፀረ ሙስና ትግሉ በኦሮሚያ ብቻ ባይገደብም ክልሉ ለሙስና ለምን እንዲህ ተጋላጭ ሆነ ብለን የኦሮሚያ ክልል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽኔር አቶ ሃምዲ ክንሶ ጠይቀናቸዉ ነበር።

በኦሮሚያ ክልል በሙስና ተጠርጥሮ ቁጥጥር ስር የሚዉሉት ግለሰቦች በሙስና ቢሳተፉም ከአስተዳደሩ ጋር የፖለቲካ ግጭት ሲፈጠር ነዉ ብለዉ አስተያየታቸዉን የሚሰነዝሩም አልጠፉም።
የኦሮሚያ ክልል ዉስጥ የሚፈፀመዉን ሙስና ለመከላከል የኦሮሚያ ክልል ሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የግንዛቤ ማስቸበጫ እየሰራ መሆኑንና በዚህም ላይ ለሙስና በር የሚከፍቱ ነገሮች ላይ ጥናትና ምርምር እያደረጉ መሆኑን ምክትል ኮምሸነሩ ተናግረዋል። ከዚህ ሌላ የባለስልጣናትና የሰራተኞች ንብረት ምዝገባ ላይ እየሰሩ መሆናቸዉን ገልፀዋል።
No comments:
Post a Comment