በአባይ ግድብ ሰበብ በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች እየተዟዟረ ለኢትዮጵያውያን ቦንድ የሸጠው የኢትዮጵያ መንግስት ገንዘቡን እንዲመለስ ተፈረደበት::
የአሜሪካን የቦንድ ሽያጭ የሚቆጣጠረው መስሪያ ቤት (The Securities and Exchange Commission) ዛሬ ባወጣው መግለጫው የኢትዮጵያ መንግስት በአሜሪካን ሃገር እየተዟዟረ የሸጠው ቦንድ ህገወጥና ያልተመዘገበ የሃገሪቱን ሉአላዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው::
በአባይ ቦንድ ሰበብ የኢትዮጵያ መንግስት በአሜሪካ ቦንድ በመሸጥ 5.8 ሚሊዮን ዶላር የሰበሰበ ሲሆን የአሜሪካን የቦንድ ሽያጭ የሚቆጣጠረው መስሪያ ቤት (The Securities and Exchange Commission) ባቀረበው ክስ መሰረት የኢትዮጵያ መንግስት ገንዘቡን እንዲመልስ ተፈርዷል:: የኢትዮጵያ መንግስት በአሜሪካ የቦንድ ሽያጭ ማድረጉን ማመኑንም ኮሚሽኑ በድረገጹ ያወጣው መረጃ ይጠቁማል::
የኢትዮጵያ መንግስት የአሜሪካንን ህግ ሳያጠና በደመነፍስ በየከተማው ዞሮ የሸጠውን ቦንድ ገንዘብ ከመመለሱም በላይ ቅጣት የተጣለበት መሆኑን ያስታወቀው የኮሚሽኑ መስሪያ ቤት ድረገጽ ከተበደረው ብድር ላይ ተጨምሮ ከነቅጣቱ 6.5 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍል ተስማምቷል::
በኮሚሽኑ ክስ ላይ እንደቀረበው የአዲስ አበባው መንግስት ከ3100 ኢትዮጵያውያን በአባይ ቦንድ ሰበብ ዶላር ሰብስቧል::
ሕወሓት የሚመራው መንግስት በአሜሪካ ቦንድ ለመሸጥ ሲንቀሳቀስ በርካታ ምሁራን ድርጊቱ ሕገወጥ ነው በሚል ሲቃወሙ; የተለያዩ አስተያየቶችንም ሕግ እያጣቀሱ በዘሐበሻ ድረገጽ ላይ ሲጽፉ እንደነበር ይታወሳል:::
No comments:
Post a Comment