Friday, June 17, 2016

በውቕሮ ከተማ የኤሌትሪክ ፓሎ ወድቆ ገመድ በመበጠሱ 9 ሰዎች ገደለ።



በውቕሮ ከተማ የኤሌትሪክ ፓሎ ወድቆ ገመድ በመበጠሱ 9 ሰዎች ገደለ።
ዛሬ ዓርብ 10/10/2008 ዓ/ም ከሰዓት ውቕሮ ከተማ ዶንጎሎ መናፈሻ በሚባል ኣከባቢ መተበጠሰው የኤሌትሪክ ገመድ በፈጠረው ኣደጋ 6 ሴቶችና 3 ወንዶች በድምሩ 9 ሰዎች ወድያውኑ ለህልፈተ ሂወት መዳረጋቸው ታውቀዋል።
በኣደጋው ኣንድ ህፃን ኣዝላው ከነበረችው እናቱ ተኣምር ሊባል በሚችል መልኩ ከኣደጋው በሂወት ተርፈዋል።
ለሁለት ፓሎዎች በመውደቃቸውና የኤሌክትሪክ ገመድ መቆረጥ የኣደጋው መነሻ በከተማዋ መዝነብ የጀመረ ቀላል ዝናብ መሆኑ ተገልፀዋል።
በክስተቱ የውቕሮ ህዝብ እጅግ ኣዝኖ እንደሚገኝና በፓሎዎች እርጅና በከተማዋ ሊከሰት የሚችል ኣደጋ ስጋት ላይ ወድቀዋል።
ባለፈው ወር ከውቕሮ በስተ ምዕራብ የምትገኝ በዓቲ ዓኾር ቀበሌ በኤሌክትሪክ ቃጠሎ ምክንያት 4 ሰዎች በቀጥታ ሲሞቱ ከ30 በላይ ኑዋሪዎች በከባድ ተጎድተው ሆስፒታል እንደገቡ ይታወቃል።
የመብራት ሃይል ትራንስፎርመሮች፣ የኤሌክትሪክ ገመዶችና ምሰሶዎች ወይም ፓሎዎች ያረጁና ጥራት የጎደላቸው በመሆኑ በሰው ሂወትና በንብረት ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ።
መብራት ሃይል 4 ሚልዮን ዶላር ዋጋ የተከፈለበት ህንድ ተጠቅማ የጣለችውና ቀለም ቀብታ የሸጠችልን ትራንስፎርመር መያዙ የሚታወቅ ነው።
የሙስና ጉዳት የብር መዘረፍ ብቻ ኣይደለም። በያንዳንዱ ዜጋ ሂወት በቀጥታም በተዘዋዋሪም ከፍተኛ ኣሉታዊ ተፅእና ያሳድራል።
በውቕሮ ከተማ በኤሌክትሪክ ኣደጋ የሞቱት ዜጎች በኣደጋው በመቃጠላቸው ማንነታቸው ለማረጋገጥና ለማወቅ ኣስቸጋሪ እንደሆነ እየተገለፀ ነው።

No comments:

Post a Comment