በቂሊንጦ የቀጠሮ እስረኞች ማቆያ የፓለቲካ እስረኞችን ጨለማ ክፍል ለይቶ በማስቀመጥ መቅጣት የተለመደ አሰራር ነው። በተለይ ደግሞ እስረኞች በእስር ቤቱ አስተዳደር የሚደርስባቸውን በደል እና መድሎ ለፍርድ ቤት ወይም ለሚዲያ እንዲደርስ ካደረጉ ወይም የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን ከጠየቁ ወደ ጨለማ ቤት ለቅጣት መላካቸው አይቀሬ እንደሆነ ይነገራል።
በ28/9/2008 አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎች የኦፌኮ አመራር አባላት ኦሮሚያ ክልል ላይ በተነሳው ተቃውሞ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማቸውን ሃዘን ለመግለፅ ጥቁር ልብስ ለብሰው ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ መውጣታቸውን ተከትሎ የቂሊንጦ እስር ቤት አስተዳደር ጥቁር ልብስ ለብሰው ፍርድ ቤት አይሄዱም በማለት ከችሎት እንዳስቀሯቸው ይታወቃል፡፡ በተከታዩ ቀጠሮም ጥቁር ልብሳቸውና ሌሎች ልብሶቻቸው በብርበራ ወቅት በመቀማታቸው በፓካውት እና በቁምጣ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወሳል። ከፍርድቤት ሲመለሱም አራቱን ከፍተኛ የኦፌኮ አመራሮች ጨለማ ቤት በመግባታቸው ቤተሰብ ሳያገኛቸው ተመልሰዋል።
በተመሳሳይ ቀን ቀጠሮ የነበራቸው ከኦሮሚያ ክልል ህዝባዊ አመጽ ጋር በተያያዘ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው 16 ሰዎች ከአምቦ ተይዘው የመጡ እና 11 የመድወላቡ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ጥቁር ልብስ በመልበሳቸው ምክንያት በቀጠሯቸው ቀን ፍርድ ቤት ሳይወሰዱ ቀርተዋል። ይህ በሆነ በማግስቱ (29/9/2008) በግቢው ከሚገኙ ሶስት ዞኖች ውስጥ ከሁለቱ ስድስት የፓለቲካ እስረኞች አስተዳደር ቢሮ እንደሚፈለጉ ከተነገራቸው በኋላ እነ በቀለ የሚገኙበት ጨለማ ክፍል እንዲገቡ ተደርጓል። የተሰጣቸው ምክንያት “እስረኞችን እያሳመፃችሁ እና እያደራጃችሁ ነው” የሚል ነው። አስሩ የፓለቲካ እስረኞች ብቻ ተዘግቶ የሚውል እና የሚያድር አንድ ጨለማ ክፍል ውስጥ እንዲኖሩ ከተደረጉ ብዙ ቀናት ተቆጥረዋል። በቀን ለ2ት እና 3ት ደቂቃ ለምታክል ጊዜ ምግብ ከሚያቀብሉ ቤተሰቦች ጋር ብቻ ነው ለመገናኘት የሚፈቀድላቸው ሲሆን ከቤተሰብ ውጪ የሚመጡ ጠያቂዎች በእስር ቤቱ ፓሊሶች ” የት/መቼ/እንዴት ነው ምታቀው/ቂው? ” ፣”ምንሽ/ህ ነው?” እና መሰል የምርመራ ጥያቄዎችን ያቀርቡላቸውና እንደሁኔታው ለ2 ደቂቃ ለመገናኘት ሊፈቀድላቸውም ላይፈቀድላቸው ይችላል። ” ለብቻችሁ ያደረግናችሁ ሆን ብለን ከሌሎች እስረኞች ልናገላችሁ ስለፈለግን ነው” የተባሉ ሲሆን

አስሩ የፓለቲካ እስረኞች ፤
1. በቀለ ገርባ ፣
2. ጉርሜሳ አያና፣
3. ደጀኔ ጣፋ፣
4. አዲሱ ቡላላ፣
5. ዮናታን ተስፋዬ፣
6. አበበ ኡርጌሳ፣
7. ፍቅረማርያም አስማማው፣
8. ብርሃኑ ተ/ ያሬድ፣
9. ማስረሻ ታፈረ እና
10. መሰለ መሸሻ ናቸው።
1. በቀለ ገርባ ፣
2. ጉርሜሳ አያና፣
3. ደጀኔ ጣፋ፣
4. አዲሱ ቡላላ፣
5. ዮናታን ተስፋዬ፣
6. አበበ ኡርጌሳ፣
7. ፍቅረማርያም አስማማው፣
8. ብርሃኑ ተ/ ያሬድ፣
9. ማስረሻ ታፈረ እና
10. መሰለ መሸሻ ናቸው።
በተመሳሳይ መልኩ የሰማያዊ ፓርቲ የጎንደር አስተባባሪ የነበረው አግባው ሰጠኝ በታሰረበት ቂሊንጦ ግንቦት 9/2008 ዓ.ም ‹‹ዘረኞች›› ብለህ ሰድበኸናል በሚል የሁለት ወር የጨለማ ክፍል እስር በእስር ቤቱ አስተዳደር ተፈርዶበት ከግንቦት 17/2008 ዓ.ም ጀምሮ ለብቻው ጨለማ ክፍል ውስጥ ይገኛል። አግባው ግንቦት 11/2008 ፍርድ ቤት በቀረበበት ጊዜ የቂሊንጦ እስር ቤት አስተዳደር ግፍ እያደረሰብኝ ነው ሲል አቤቱታ አሰምቶ የነበረ ሲሆን ‹‹ጨለማ ቤት እናስገባሃለን›› እያሉ እንደዛቱበትም በወቅቱ ገልጾ ነበር፡፡
★ማንኛውም አይነት ጥቁር ልብስ ለማንኛውም እስረኛ እንዳይገባ የተከለከለ ሲሆን ቀደም ብሎ የገባም ተሰብስቦ እንዲወጣ እየተደረገ ነው።”

No comments:
Post a Comment