የኣብራሃ ደስታ ችሎት
፷፷፷፷፷፷፷፷፷
፷፷፷፷፷፷፷፷፷
ጀግናው ኣብራሃ ደስታ በቃሊቲ እስርቤት እየማቀቀ ይገኛል።
ከትናንት በስትያ ከ2 የትግል ጓደኞቼ ልንጎበኘው ሄድን።
የወህኒ ቤቱ ሃላፊዎች “ኣብራሃ ደስታ ከቅርብ ቤተሰቦቹ በስተቀር ለማንም እንዲጎበኘው ኣይፈቀድም ብለው ከለከሉን።
የወህኒ ቤቱ ጠባቂዎች ኣብራሃ ደስታ መጎብጀት ኣይቻልም ያሉበት ምክንያት ኣስረዱን ብንላቸው “በቃ ትእዛዝ ነው” ብለው መለሱን።
ኣብየቱታ ለማቅረብ እስከ 08:00 ጠብቀን ከትግራይ መምጣታችን ነግረን እንዲፈቅዱልን ብንጠይቅም ሰሚ ኣጣን።
ኣብራሃ ደስታ በኣካል ኣግኝቼ ባላዋራውም በነጋታው ግንቦት 30/ 09 / 08 ዓ/ም ወደ ችሎት ሲያቀርቡት ኣምስት ኪሎ በሚገኘው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተገናኝተናል።
ፍርድ ቤቱ እንደተለመደው ለሰኔ 28 / 09/ 08 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ብሎ ኣልፎታል።
ኣብራሃ በፊቱ የጀግነት፣ ኣልበገር ባይነትና ተስፋ ይነበብበት ነበር። ጤንነቱም መልካም እንደሆነ ከፊቱ ይነበባል።
ስለ ጤንነቱ የምትጨነቁ ወገኖች ደህና መሆኑ ላበስራቹ እፈልጋለው።
ስለ ጤንነቱ የምትጨነቁ ወገኖች ደህና መሆኑ ላበስራቹ እፈልጋለው።
የተከሰሰበት “የሽብር” ክስ ማስረጃ እንደሌለበት ፍርድ ቤቱ የሰጠው ነፃ የሚል ውሳኔ እንዳለ ሆኖ እኔን ጨምሮ ከ10 በላይ ተጋሩ ኢትዮጵያውያን በኣብራሃ “ኣሸባሪነት” የውሸት ምስክር እንድንሆናቸው በማስፈራራት፣ በማሰር፣ በመደለል ያደረጉት ጥረት ኣምክነነዋል።
ችሎቱ ኣሁንም ተለዋጭ ቀጠሮ በመያዝ የፍርዱ ሂደት እያጓተተው ይገኛል።
ጀግናው ሰለማዊ ታጋይ ኣብራሃ ደስታ መንግስት ሃሳቡ ካልቀየረ ሓምሌ 01/ 11/ 08 ዓ/ም ከወህኒ ቤቱ ይወጣል።
ነፃነታችን በእጃችን ነው
No comments:
Post a Comment